ሰበር መረጃ! 13 ጀነራል መኮንኖች ተባረሩ!

13 ጄኔራል መኮንኖች ከሰራዊቱ ተሰናበቱ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2

የሀገር መከላከያ 13 ጄኔራል መኮንኖች ከሰራዊቱ በጡረታ ተሰናበቱ።

ፋይል ጄኔራል መኮንኖቹ በጡረታ የተሰናበቱት የሐገር መከላከያ ሰራዊትን በተሻለ አደረጃጀት ለማዋቀር የተጀመረውን መርሃ ግብር ተከትሎ መሆኑ ታውቋል።

ከሃገር መከላከያ ሰራዊት በጡረታ ከተገለሉት መካከል ሜጄር ጄኔራል በርሃነ ነጋሽ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሃላፊ የነበሩ፣ሌተናል ጂኔራል ሃለፎም እጅጉ የመከላከያ ኮሌጅ አዛዥ፣ሜጄር ጄኔራል ሙሉ ግርማይ ከመከላከያ ሎጅስቲክ ተጠቃሽ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

በጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጄኔራል ሰአረ መኮንን ፊርማ በጡረታ ከተሰናበቱት 13 ጄኔራል መኮንኖች ውስጥ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ሜጀር ጄኔራል ዮሐንስ ወልደ ጊዮርጊስ፣ሜጀር ጄኔራል አትክልቲ በርሄ፣ሜጀር ጄኔራል ኢብራሒም አብዱል ጂላል፣ሜጀር ጄኔራል ገብሬ ዲላ በተመሳሳይ በጡረታ ተሰናብተዋል።

ቀደም ሲል ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም እንዲሁም ሜጄር ጄኔራል መሐሪ ማአሾ በጡረታ መሰናበታቸው ታውቋል።

በሐምሌ ወር መጨረሻ በመከላከያ ስታፍ ኮሌጅ የሰለጠኑ ከፍተኛ መኮንኖች በተመረቁበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመከላከያ ውስጥ ጠንከር ያለ ሪፎርም መጀመሩን መግለጻቸው ይታወሳል።

የመከላከያው አዲስ አደረጃጀትን በማስጠናት ጄኔራል ሰአረ መኮንን ለመንግስት ማቅረባቸውን ገልጸው በጥናቱ መሰረት ተግባራዊ ርምጃ እንደሚቀጥል አስታውቀው ነበር።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.