የአፋን ኦሮሞ ኘሮግራሞች በETV ተጀመረዋል !

hqdefaultትዮጵያቭዥን ተቋርጦ የነበረው የአፋን ኦሮሞ ፕሮግራም ስርጭትን ጀመረ
=========================================
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከ10 ዓመታት በፊት ተቋርጦ የነበረውን የአፋን ኦሮሞ ፕሮግራም ስርጭትን ዛሬ በቡራዩ ከተማ ጉቴ ሆቴል በተደረገው የመክፈቻ ፕሮግራም ጀምሯል፡፡

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሸን የቴሌቭዥን ዘርፍ ምክትል ስረ አስፈፃሚ አቶ አቤል አዳሙ እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም በአፋን ኦሮሞ ሲተላለፉ የነበሩ እንደ ደንጋ ያሉ አዝናኝ ፕሮግራሞች ቋንቋውን የማይችሉ ሰዎች ጭምር የሚያዝናኑ ስለነበሩ የፕሮግራሙ በድጋሜ መከፈት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በበኩላቸው፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሲተላለፍ የነበረው የአፋን ኦሮሞ ስርጭት መቋረጥ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸው፣ አሁን በድጋሜ ስርጭት መጀመሩ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ዶ/ር ተናግረዋል፡፡ የአፋን ኦሮሞ ስርጭት በEtv Languages ቻናል ላይ የሚተላለፍ ሲሆን፣ በቀን የ4 ሰዓት ስርጭት ይኖረዋል፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.