ጀዋር እና የመጨረሻ አላማው…

FB_IMG_1537942323154

ኦነግንና ኦፌኮን በግፊት ለማዋሃድ ከሚደረገው እሩጫ ጀርባ ያደፈጠው የጃዋር ሴራ!!
ጃዋር፣ እኔ ስልጣን ላይ ካልወጣሁ ‘የቄሮ መንግስትን’ ይዤ አገር እገነጥላለሁ እያለ ከማቅራራት አልፎ፣ የስልጣን ጥሙ ማሳኪያ የትሮይ ፈረስ ባደረገው በቀለ ገርባ ጀርባ ተከልሎ በመሰረታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች የማይግባቡትን ኦነግንና ኦፌኮን በግፊት በማዋሃድ በኦሮሚያ ክልል ተቀናቃኝ የሌለው የጃዋርን ፅንፈኛ ዘረኝነት የሚያራምድ የፖለቲካ ድርጅት ለመመስረት እየተንቀሳቀሰ ነው
ለአማራው ችግር መፍትሄ እሰጣለሁ’ እና ‘የቄሮ መንግስት እኔ ነኝ’’ በሚል ወደር የለሽ ትዕቢት፣ ዘረኝነቱና ከፋፋይነቱ የታወቀው ጃዋር በከፍተኛ ግፊት የፖለቲካ ፕሮግራማቸው አብሮ ለመሄድ የማይችሉትን ኦፌኮንና ኦነግን በከፍተኛ ግፊት በማዋሃድ ፣ በአሁን ወቅት የጃዋር እኩይ ተልዕኮ ተባባሪ እየሆነ ካለው በቀለ ገርባ በኩል በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው፣ የሰከነ ፖለቲካ አራማጁ፣ ጉምቱው እና አንጋፋውን ኦሮሞ ፖለቲከኛዶ/ር መራራ ጉዲናን ከኦፌኮ መሪነት የማባረር እና የፓርቲውን መዋቅር በእጅ አዙር የመቆጣጠር መሰሪ አላማ እንዳለው ተደርሶበታል።
የጃዋር ፖለቲካ ሴራ ሌላው ተጠቂ የሚሆነው የሸኔ ኦነግ ሊቀመንበር የሆነውን ዳውድ ኢብሳም ተመሳሳይ መልኩ ከድርጅቱ በማሶገድ ፣ ኦፌኮ በመላው ኦሮሚያ ያለውን አደረጃጀት እንዲሁም የኦነግን አክራሪ ብሄረተኝነትና የታጠቀ ሀይል በአንድ የሚይዝ ግዙፍ ፓርቲ ለማቋቋም አልሞ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ታውቋል።
በእበላ ባይነት ተታሎ የጃዋርን የጥፋት ህልም ለማሳካት መሳሪያ እየሆነ ያለው የ60 አመት አዛውንቱ በቀለ ገርባ ነው፡፡ጃዋር አይደለም ሀገር መምራት እራሱን መምራት የማይችል ደካማ ነው።
ጃዋር ሆይ ማወቅ ያለብህ ግልፅ ጉዳይ መቀሌ የመሸገው ቀልባሽ ሀይል የከፈተብንን ሁሉን አቀፍ የፀረ-ለውጥ ጥቃት ለመመከት በምንቀሳቀስበት በዚህ ወቅት ከቀልባሾቹ ጋር በጥምረት ለመስራት የምያታደርገውን እያንዳንዷን መሰሪነት እንደምናውቅ ነው።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.