ዶር አብይ በ11ኛው የኢህዴግ ጉባዔ ላይ ከተናገሩት

“ከመደመር የተሻለ አማራጭ የለንም:-

* እንደ ኢትዮጵያ ላለችና ፈርጀ ብዙ ብዝኃነትን ለተላበሰች ሀገርፌዴራሊዝም የተሻለ የአስተዳደር ሥርዓት ነው።

የፌዴራልመንግሥት አወቃቀሩ ደግሞ የሀገሪቱን ታሪካዊና ነባራዊ ሁኔታግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት።

* ክልላዊ አስተዳደርን ከብሔር ማንነት ጋር ሳናምታታ ማስተናገድከቻልን እንደኛ ሀገር ላለ ነባራዊ ሁኔታ ፌዴራሊዝም ተመራጭየአስተዳደር ስርአት መሆኑ አያጠያይቅም።

* ክልላዊአስተዳደሮች በክልላቸው የሚኖሩትን ሁሉንም ግለሰቦችናሕዝቦች በእኩልነት የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለባቸውም።

* ይህ ሲሆን ዜጎች በየትኛውምየሀገራችን ክፍል ያለስጋት ተንቀሳቅሰው መስራት እና ሀብትማፍራት የሚያስችላቸውን ትምምን ስለሚያገኙ አብሮነታቸንይበልጥ እየጠነከረ የምናስባትን ጠንካራ ሀገር መስራትእንችላለን።

* በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትርክት ውስጥ የብሔር ማንነት እና ኢትዮጵያዊ ማንነት እስካሁን ድረስ ሚዛን ጠብቀው መሄድአልቻሉም።

* ሁለቱን ማንነቶች እንደሚተባበሩ ማንነቶችሳይሆን እንደሚተካኩ ማንነቶች የማየት ዝንባሌ ተፈጥሮቆይቷል።

* በቀጣይ ግን እነዚህን ሁለት ማንነቶች ሚዛንአስጠብቀን ለማስቀጠል የሕዝብ ለሕዝብ መድረኮች፣ የባሕልትውውቆችና ሌሎችም ኅብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያንየሚያሳዩ እሴቶችን ከፍ ከፍ ለማድረግ ርብርብ መደረግይኖርበታል።

* በዋናነት ፉክክራችን ከዓለም ጋር እንጂ እርስ በርሳችን ሊሆንአይገባም።

* ከዓለምም ጋር ስንፎካካር በመጠፋፋት መንፈስሳይሆን ለሁላችንም የምትሆን የተሻለች ዓለምን በመገንባትበቀና መንፈስ ላይ መሆን ይኖርበታ::“

“A Federal form of government is a preferred option in Ethiopia as long as we don’t confuse regional administrative arrangements with ethnic identity for we should recognize each regional administrative unit should serve all citizens with respect, equality and without discrimination.”

Prime Minister Abiy Ahmed at EPRDF 11th Congress, Hawa

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.