የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በይፋ ስራ ጀመረ

የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በይፋ ስራ ጀመረ
*********************

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ዛሬ በይፋ ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሁለት ወራት በፊት የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ እንዲቋቋምና ገንዘብ ማሰባሰብ እንዲጀምር ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ በቀን 1 ዶላር ለኢትዮጵያ ገቢ የሚያደርጉ ከሆነ በችግር ውስጥ ያሉ የበርካታ ኢትዮጵያውንያንን ኑሮ መቀየር ይቻላል ብለው ነበር፡፡

በዚህም መሰረት የዳያስፖራ የትረስት ፈንድ ተቋቁሞ ገንዘብ የማሰባሰብ ስራን ዛሬ በይፋ ጀምሯል፡፡

የገንዘብ ገቢ ማድረጊያ የሒሳብ ቁጥር 1000255726725 ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ በሒሳቡ ቁጥሩ ገቢ ማድረግ እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.