በ13.8 ቢሊየን ብር ስምምነት

ባለስልጣኑ በ13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የስምንት የመንገዶች ግንባታ ለማከናወን ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በ13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር 600 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ ስምንት መንገዶችን ለማስገንባት የኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ።

መንገዶቹ ከዚህ በፊት በጠጠርና በእስፋልት ደረጃ የነበሩ ሲሆን፥ካላቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንፃር ታይቶ በአስፋልት ደረጃ እንዲገነቡ የውል ስምምነቱ እንደተፈረመ ተነግሯል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው ወደ አስፋልት ደረጃ የሚያድጉ መንገዶችም፦

አድርቃይ -ጠለምት፦ 76 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር፣

እስቴ- ስማዳ፦ 53 ነጥብ 08 ኪሎ ሜትር፣

ጣርማ በር-መለያ-ሰፊሜዳ መለያ- ሞላሌ-ወገሬ፦ 118 ነጥብ 87 ኪሎ ሜትር፣

መሰል- ኮራቴሩ ሎት 1፦ 84 ነጥብ 02 ኪሎ ሜትር፣

መሰል-ኮራቴሩ ሎት 2፦ 72 ነጥብ 34 ኪሎ ሜትር፣

ጅማ-አጋሮ-ዴንዴሳ ወንዝ፦ 79 ነጥብ 07 ኪሎ ሜትር፣

አርሲ-ሮቤ-አጋርፋ-አሊ፦ ኮንትራት 1 አሊ ከተማ-ዋቤ ድልድይ፣ 53 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር እና ውቅሮ-አፅቢ ያልተገለፀ መንገዶች ናቸው።

ከጅማ-አጋሮ-ዴንዴሳ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ውጭ ያሉት መንገዶች ከጠጠር ወደ አስፋልት የሚያድጉ መሆናቸውን የመንገዶች ባለስልጣን ያስታወቀ ሲሆን፥ የመንገዶቹ ግንባታ በስድስት የሀገር ውስጥና የውጭ ግንባታ ተቋራጮች የሚፈፀም ነው ተብሏል።

የመንገዶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅም በአካባቢዎቹ የሚመረቱ ጤፍ፣ ስንዴ እና ፍየል እንዲሁም ሌሎች ምርቶችን በቀላሉ ወደ ገበያ ማውጣት የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.