ትግራይ ለተመደባቹ ተማሪዎች

ከሌሎች ክልሎች ወደ ትግራይ የሚመጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምንም አይነት ችግር እንደማይገጥማቸው የትግራይ ክልል መሪ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ገለጹ:: “የተረጋጋ ሁኔታ ከሌለ ተማሪዎች በአግባቡ መማር አይችሉም:: ለዚህም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩንቨርስቲዎችና በክልሉ መንግስት ዝግጅት ተደርጓል” ያሉት ዶ/ር ደጺ “ከዚህ በፊት ባሉት ዓመታት በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማሩን የሚያውኩ ሁኔታዎች ብዙም አልተስተዋሉም:: ሆኖም ችግሮች አይከሰቱም ተብሎ ስለማይታለፍ እንደ መንግስት ተቋማቱ ሰላማዊ እንዲሆኑ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎል:: ተማሪዎችም ችግሮች ካሉ ተወያይተውና ተነጋግረው እንደሚፈቱ እምነቴ ነው” ብለዋል::

“በዘንድሮው ዓመት በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ችግር እንዳይፈጠር ምክክር ተደርጓል:: የትግራይ ህዝብ ዘርና ቋንቋ ሳይለይ ሁሉንም አክባሪ ነው:: ህብረተሰቡ በትምህርት ተቋማት ያሉ ተማሪዎችን አክብሮና ደግፎ ያቆያል:: ተማሪዎችም ችግሮች ካሉ በአግባቡ ለሚመለከተው አካል አለባቸው እንጂ የሚነሱትን ችግሮች ወደ ብሄርና እምነት በመውሰድ ችግር መፍጠር አያስፈልግም” ያሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት ከየትኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ልጆቻቸውን በክልሉ ወደሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚልኩ ወላጆች ስጋት ሊፈጠርባቸው እንደማይገባና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደላኳቸው አድርገው እንዲወስዱም ጠይቀዋል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.