በህዋሀት ላይ የተጀመረው የኢኮኖሚ እቀባ

ህወሀት ከወዲሁ ከተለያየ አቅጣጫ አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ ይገኛል

እጅግ አሳዛኝ መንገዶችን በመከተል ለሀያ ሰባት አመታት የትግራይን ህዝብ በማይሆን መንገድ መምራት ብቻ ሳይሆን ከሁሉም የኢትዮጵያ ጋር በማጋጨት የማይሆን የመሬት ነጠቃና ወረራን በመፈፀም አስቀያሚውን የዘር ጭፍጨፋ በአማራ በጋምቤላ እና በአፋር ላይ ፈፀመ።

ዛሬ ግን ህወሀት ከያቅጣጫው ከባድ ፈተና ገጠመው የወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ደፋ ቀና የሚለው ህወሀት ነገሮች እንዳሰበው ሊሆኑለት አልቻሉም በከፍተኛ ፍጥነት ከመሳሪያ እስከ ኢኮኖሚ ማዕቀብ በሶስቱ ክልሎች አደጋ ገጠመው በተለይ በአማራ ክልል የገጠመው ፈተና ከባድ ነው የክልሉ ህዝብ ህወሀት እንዳነሳው ጦር አላነሳም አልገደለም ነገር ግን ከትግራይ ጋር ያለውን ግንኙነት መንገድ በመዝጋት አቆመ በመሳሪያ ግድያ ያመነውን ህወሀት የአማራ ህዝብ እሽ እሱ ካዋጣ እኛ ግን ግንኙነት እንዲኖረን አንፈልግም በማለት በሰላም መንገድ በመዝጋት አቆመ።

ከአፋር በኩል ደግሞ አስገራሚ ነገር ተሰማ አፋር ከእንግዲህ ዝም አይልም በሚን ከባዱን ትግል ተቀላቀለ. የአማራ ክልል ሲዘጋ ረጅሙ እና አድካሚው ትራንስፖርት ያለው በአፋር በኩል ነው ያንም ሙሉ ለሙሉ የአፋር ህዝብ ዘጋው ።

አስተውሉ ሁለቱም ክልሎች ጦር አልሰበቁም እንደህወሀት ሰው አልገደሉም በቃ መንገዳቸውን ዘጉ በሰላም።

ህወሀት አሁን መራወጥ ጀምሮዋል የአማራን ህዝብም ሆነ የአፋርን ህዝብ ምንም ማለት አይችልም በቃ በሰላም ግንኙነታቸውን አቆሙ።

የሽማግሌወቹ ህወሀታውየን ካምፕ ዛሬም አልሰለጠኑም ግልብ የሆነ አመለካከት አላቸው ጭራሽ በራሳቸው ጥፋት የአማራን ህዝብ እና የአፋርን ህዝብ መኮነን ጀመሩ ሆኖም የአፋር እና የአማራ ህዝብ የወሰደው እርምጃ ሰላምን ነው።

63% የትግራይ ኢኮኖሚ በአማራ ህዝብ ላይ የቆመ ነው ዛሬ ላይ ህወሀት ልትደብቀው የሞከረችው ማፈን ዘመቻ ከትግራይ ህዝብ ፈንቅሎ እየወጣ ነው የትግራይ ፋብሪካወች ስራ የለም አቅርቦቱ ከአማራ ክልል ሙሉ ዝግ ነው በየመንገዱ ጭነት የጫኑ መኪኖች ቁመዋል መንገድ ዝግ ነው በአፋር በኩልም የመጨረሻው መስመር ዝግ ነው መኪኖች ለቀናት ቆመዋል ።

ህወሀት ሶስት አማራጭ አላት

1• በሰላም የሁለቱን ጥያቄ መመለስ ከሁለቱ ክልሎች የወሰደችውን መሬት ማስረከብ

2• ሙሉ በሙሉ ከሁለቱ ክልሎች ጋር ግንኙነት አቁማ መገለል የትግራይን ህዝብ ለመከራ መዳረግ

3• እንደለመዱት የትግራይን ህዝብ ለድጋሜ የማያልቅ ጦርነት መማገድ።

አሁን የአማራም ሆነ የአፋር ህዝብ በጣም የሰለጠነ መንገድ ነው የተጠቀሙት ህወሀት ገላም አፍናም ቢሆን ትልቅ እድል ሰተዋታል።

ጥፋቱ ያለው ህወሀት ውስጥ ነው አይ ጦርነት ይሻለኛል ካለች ደግሞ ችግሩ የሚሆነው እራሱዋ ላይ ነው ።

ህወሀት ማወቅ ያለባት ጦርነቱ ከደርግ በራሱ ምክንያት ከፈራረሰው ጋር ሳይሆን ለህልውናው ጋር ከቆመው ከአማራ ከአፋር እና ከጋምቤላ ህዝብ ጋር ነው ይህኛው ጦርነት ለየት ይላል ህልውና የሚሉት ከባድ ጦርነት። ማብቂያ የሌለው ጦርነት ።

ምናልባት ህወሀት ያልገባት ነገር ይህን ጦርነት ብትጀምረው ከባድ የሚሆነው በህልውና ላይ የተጋረጠ በመሆኑ በቀናት ውስጥ አማራም አፋርም ጋምቤላም የህወሀትን አስር እጥፍ እንደሚሰራ ነው. ህወሀት በአፋር ጦርነት አስባ ሞክራው ነበር ባለፉት ሶስት ቀናት የገጠማት ግን የፈራረሰው ደርግን የጠላው ጦር አይደለም በየዱር ገደሉ ለሀያ ሰባት አመታት ቂም የቁዋጠረው ወገኖቹን በህወሀት ያጣው በደል የደረሰበት የደፈጣ ተዋጊ የአፋር ህዝብ ነው ። የህወሀት ጦር ሊራመድ አልቻለም በየደፈጣው የገጠመው ፈተና በቃል የሚገለፅ አይደለም እስካሁን ከ71 በላይ የህወሀት ወታደሮች በአፋር የደፈጣ ተዋጊወች ተገለዋል ይህን ግን ህወሀት ድብቅ አርጋዋለች ይህ በሆነበት በደፈጣ ውጊያ አለም የመሰከረችለት የአማራ ህዝብ ጋር ልክ እንደ ደርግ አስባ ጦርነት ማሰብ ለህወሀት ቀላል ከመሰላት ችግሩ ቀላል አይሆንም ለሀያ ሰባት አመታት ወንድም አባት ዘመድ የጨረሰችበት የአማራ ህዝብ ነው ።

በህወሀት ችግር የትግራይ ህዝብ ለድጋሜ ችግር ድህነት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ያለው ግንኙነት በእጅጉ ተስተጉዋጉሉዋል በኢኮኖሚው ላይም ህወሀት እንደለመደችው በመዋሸት ልት ደብቅ ብትሞክርም ግልፅ ሆኖ ወቱዋል።

ያለውን ችግር መፍታት ለህወሀት ትልቅ ስራ ነው

ሌላው ህወሀት ከግብፅ ጋር የለመደችውን ቁማር መሞከር ነው ይህም የኦሮሞን ህዝብ ስትገል መኖር ሳያንሳት ኦነግን አባራ ካገር አስወጥታ የነብስ አባቱዋን ግብፅን ፕሮፖዛል በመቀበል ኦነግን ምሳ አብልታ ሸኘች እናም ውጥኑዋ ከነትጥቁ ኦነግን በማስገባት ግብፅ የገቢዋ ምንጭ በማድረግ መልሳ ኦሮምያን ለመያዝ ያላትን ህልም በተዘዋዋሪ ጀመረችው ከቀድሞው ያልተማረው ኦነግ ከዚህ ቀደመ በህወሀት መከዳቱን ረስቶ ስልጣኑን በኦሮሞ ህዝብ እንደሚመራ ረስቶ በህወሀት ማታለል ሰንሰለት ውስጥ ገብቶ የራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቱዋል ።

ህወሀትም በኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣቶቹዋ መሰረት ኦነግ መስላ ቅስቀሳ በማድረግ የለማን አስተዳደር ፈተና ውስጥ በመክተት በራሱዋ በኦሮምኛ ተናጋሪወች ለመምራት ሌላ እርምጃ መውሰድ ጀምራለች ችግሩ የኦሮሞ ህዝብ እየነቃባት ኦነግን አርፈህ ተቀመጥ ዛሬ በራሳችን ልጆች እየተመራን የምን ጦርነት ነው በሚል መልስ እየተሰጠው ነው።

ወጣም ወረደ ህወሀት ግብፅን ይዛ ኦሮምያን የውድቀት መነሀሪያ በማድረግ ኦነግን ተጠቅማ ወደስልጣን እመጣለሁ ብላ ያሰበችውን ድራማ ሌሎች ክልሎች ቀድመው አውቀዋል በተለይ ጋምቤላ አፋር አማራ እና ደቡብ ክልሎች ህወሀት በፈለገችው መንገድ ትምጣ በምንም ትሂድ በራቸው ዝግ ነው ምናልባት የኦሮሞ ህዝብ እንደምናየው ኦሮሞ መስለው ኦሮምኛ ተናጋሪ አገብጋቢ ህወሀታውያን የኦሮሞን ህዝብ የሚያስጠብቁ መስለው ኦነግን በመጠቀም ኦሮምያን ወደሁዋላ ለማስቀረት የሚያደርጉት ጉዞ የኦሮሞን ህዝብ ትርጉሙ ተታሎ ኦነግን ደግፎ የለማን አስተዳደር ገፍቶ ጥሎ ህወሀት እና ግብፅ ባሰለጠነቻቸው ሞኝ ኦነጋውያን ቢመራ እና ቢቀጥል ሎሎች ክልሎች ቀድመው ስለነቁ ይሳካል ማለት ዘበት ነው።

የሚሻለው የአፋር የአማራ እና የጋምቤላ ህዝቦች የጀመሩትን የሰላም አማራጭ መቀበል ልክ ነው ።

ለአፋር ለጋምቤላ እና ለአማራ ህዝብ ያሳዩት ትልቅ ጨዋነት እና ትልቅ ትግስት እውነት ምስጋና ይገባቸዋል። የሀያ ሰባት አመቱን የመከራቸውን ጉዞ እንኩዋን ሳያስታውሱ በፍቅር ህወሀትን ለመኑ ህወሀት አልተማረም ይህም ሆኖ መንገዳቸውን ዘጉ ህወሀት ግን ጠብ አጫሪ ሆኖ እየገደለ ነው ቆይ ከዚህ በላይ የአማራ የአፋር እና የጋንቤላ ህዝብ ምን ማድረግ ነበረበት????

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.