ኢትዮጵያ በሚገቡ እቃዎች ላይሆን 90 ከመቶ ታክስ ቅነሳ …

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት ዜጎች በመዳረሻ አውሮፕላን ማረፊያ የቪዛ አገልግሎትን ጥቅምት 30 ትጀምራለች

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት ዜጎች በመዳረሻ የአውሮፕላን ማረፊያ የቪዛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን አሰራር ልትጀምር ነው።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ከጥቅምት 30 ቀን 2011 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሀገራት በመዳረሻ አውሮፕላን ማረፊያ የቪዛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን አሰራር ትጀምራለች።

በመዳረሻ አውሮፕላን ማረፊያ የቪዛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን አሰራር መጀመሩም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የቀጠናውን ሀገራት አንድነት ለማጠናከር ያላቸውን ህልም ለማሳካት እንደሚረዳ ነው አቶ ፍጹም በትዊተር ገፃቸው የገለጹት።

አገልግሉቱ የቀጠናውን ሀገራት የእርስ በእርስ እና የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው።

ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች
የአህጉሪቱን የነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነት በሩዋንዳ ኪጋሊ ከተፈራረሙት 44 የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗ ይታወሳል።

በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ያሳድጋል ተብሎ የሚታመንበት ይህ የነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነት የአፍሪካ ህብረት 2063 የአጀንዳ ዋነኛ አካል መሆኑም ይታወቃል።

ስምምንቱ በአፍሪካ አንድ የሸቀጥ እና አገልግሎት ገበያን መፍጠር ዓላማው ያደረገ ሲሆን፥ በሀገራቱ መካከል የሚካሄድን የንግድ ግንኙነት ያቀላጥፋል ተብሎ ታምኖበታል።

የነፃ ንግድ ቀጠና ስምምንቱን 55 ሀገራት መፈረም የሚጠበቅባቸው ሲሆን፥ በድምሩ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ህዝብ እና 2 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር የሀገር ውስጥ ምርት መጠን እንደሚይዝ ይጠበቃል።

ስምምንቱ ሀገራት ከሌላ የአፍሪካ ሀገር በሚያስገቡት ሸቀጥ ላይ ከጣሉት ቀረጥ ውስጥ 90 በመቶውን እንዲያነሱ ያስገድዳል።

በሂደትም ነፃ የሰዎች ዝውውርን እና የጋራ የመገበያያ ገንዘብን በጥቅም ላይ ማዋልን ያካተተ ነው።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.