የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት መጨረሻ

ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር !

ቅዳሜ ጥቅምት 24 ቀን በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ለሚኖረው ታላቅ የሙዚቃ ዝግጅት ሁለት ቀናት ብቻ ይቀሩናል።

የመግቢያ ትኬቶችን መቀየር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ አዲስ በታተሙ የመግቢያ ትኬቶች እየቀየርን መሰንበታችን ይታወቃል። የመግቢያ ትኬቱን አስቀድማችሁ ለገዛችሁና እስከዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ሄዳችሁ አዲስ በታተሙት የመግቢያ ትኬቶች የመቀየር እድሉን ያላገኛችሁ ወገኖች እስከ ነገ አርብ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።

ሰላም ያገናኘን !

አርቲስ ቴድሮስ ካሳሁን

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.