ቻይና የገነባችው ሆቴል አለምን አስገርሞዋል

ዓለም ላይ ባልተለመደ መልኩ ቻይና

በዓለም የመጀመሪያው የጥልቅ ጉድጓድ ሆቴል በሻንጋይ ተከፈተ

በቻይና በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የተገነባው ይህ ሆቴል ሀብታም ደንበኞቹ በተገኙበት ትናንት ተመርቋል፡፡

88 ሜትር ጥልቀት ካለው ጉድጓድ ውስጥ የተገነባውን ይህን ባለ 336 ክፍል ሆቴል ከጎርፍ መከላከሉ ለኢንጅነሮች ትልቅ ፈተና እንደነበር ነው የተገለፀው፡፡

በ288 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው ኢንተር ኮንቲነታል ሻንጋይ ዎንደርላንድ ከሆቴል በተጨማሪ የህዝብ መናፈሻ ፓርክም እንዳለው ተገልጿል፡፡

የሆቴሉ ጀርባ ከአንደኛው የጉድጓዱ ግድግዳ ጋር ተለጥፎ የተሰራ ነው፡፡ ከፊት ለፊቱ ካለው ሌላው የጉድጓዱ ግድግዳ ደግሞ ፏፏቴ ቁልቁል ሲወርድ ይታያል፡፡

ከመሀል ሻንጋይ ተነስቶ ከዚህ ባለ 17 ፎቅ ሆቴል ለመድረስ በመኪና የአንድ ሰዓት ጉዞ ይጠይቃል፡፡ አንድ ክፍል ለአንድ ሌሊት ለመከራየት ቢያንስ 490 ዶላር ወይም ከዚያ በላይ እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- asiaone.com

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.