እነ ጀዋር በትላንትናው እለት ትልቅ ድራማ ሰርተዋል

ትላንት ስውር ዘመቻ ነበር…
የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሹመት የፀደቀው ከዕለተ ረቡዕ ጀምሮ የተቀናጀ ዘመቻ በማድረግ በዕለተ ሐሙስ በሚሰየመው የፓርላማ ስብሰባ የፓርላማው አባላት እንዳይገኙ ውስጥ ለውስጥ ለእያንዳንዱ የኦዴፓ ተወካይ የፓርላማ አባል ስልክ በመደወል ጫና ለማድረግ የሞከሩት እራሳቸውን ሁለተኛ መንግስት አድርገው የሚቆጥሩት አካላት ጥረት ክሹፍ በመሆኑ ነበር።

ይህ ደካማ ሙከራ ያን ያህል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ባይሆንም እንደዚህ ላለው አፍራሽ አላማ ለመተባበር በማሰብ በፓርላማው ስብሰባ ሳይገኙ የቀሩ አባላትን በተመለከተ በራሱ በዶ/ር አብይ የሚመራው ኦዴፓም ሆነ ፓርላማው ትምህርት ሊወስዱበት የሚገባ ይመስለኛል። ምንም እንኳን ፓርላማው በህግ የተቀመጠውን ምልአተ ጉባኤ አሳክቶ በያዘው አጀንዳ መሰረት ሹመቱን ማፅደቅ ቢችልም። ከስውር ዘመቻው ጀርባ ቆመው በርከት ያሉ መቀመጫዎችን ክፍት ያደረጉ አባላት እንደነበሩ ተስተውሏል። ከ547 የፓርላማ መቀመጫ የተገኙት 330 ሲሆኑ ከተገኙት አባላት መካከል ቱ4 ሲቃወሙ 3ቱ ድምፅ ተአቅቦ ከማድረጋቸው በቀር ሹመቱ በከፍተኛ አብላጫ ድምፅ ለመፅደቅ ችሏል።

የተለመደ የፓርላማ አባላት መዝረክረክ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ወቅት በዛ ያሉ አባላት ከመቀሌ አዲስ አበባ መምጣት ፈርተው የተደበቁ፤ በአምባሳደርነት የተሾሙ እና ያልተገኙ፤ በህመምና በሞት ከአባልነት የተቀነሱ፤ የሸፍጥ ዘመቻውን በመተባበር እና በመፍራት የቀሩ ተደምረው ወደ 210 የሚደርሱ አባላት በስብሰባው አልተገኙም። ፓርላማው ትምህርት ይውሰድ ያሰኘኝ ይሄው ነው።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.