ኢትዮጵያ የአረጁ አስተሳሰቦችን በማስወገድ ላይ ትገኛለቸ

“የኦሮሞ ህዝብ ሆይ አስከመቼ የህዉሀትና የህዉሀት ተላላኪዎች መጫወቻና አሻንጉሊት እንሆናለን!!!የስልጣና ጥማት እንጂ የኦሮሞ ህዝብና ወጣት የከፈለዉ መስዋትነት ያላስጨነቃቸዉ እንደ ዳዉድ ኢብሳ አይነት ግለሰቦች እንደ ካርታ እየመዘዙ ሲጫወቱብን የምንፈዘው ለምን ይሆን???ቄሮ በህዉሀት ትእዛዝ በመሳሪያ ሲያልቅ የኦሮሞ ሴቶች በደህንነቶች እየታፈኑ በህዉሀት ባለስልጣናት ሲደፈሩ አባገዳዎች ታፍሰዉ ማእከላዊ ሲሰቃዩ ዳዉድ ኢብሳ አንድ ቀን እንኳን ለመቃወም ሞክሮ ያዉቃል??አንድ ቀን እንኳን የወገኑ ደም አሳዝኖት መግለጫ ሰጥቶ ያዉቃል???እኛ ደማችንን ስናፈስ የኦሮሞ እናቶች ሲያለቅሱ ቄሮዎች ሲሞቱ ዳዉድ ኢብሳ ኤርትራ ዉስጥ በወር 400000ብር በሚከፈልበት ቤት ዉስጥ ሲዝናና እና አለሙን ሲቀጭ ነበር እኮ ወንድሞቼ!!ጭራሽ የንቀቱ ብዛት ከገዳዮቻችንና እህትና ወንድሞቻችንን ከደፈረዉ አረመኔዉ ህዉሀት ጋር መቀሌ ላይ ቁርጥ ስጋ አየተጎራረሰና ወይን እየተራጨ አሳይቶናል እኮ ዳዉድ!!አብይ ስልጣን ከመያዙ ጥቂት ወራት በፊት እንኳን በህዉሀት ትእዛዝ በአሰቃቂ ሁኔታ ሞያሌ ላይ የተረሸኑት የ30 የኦሮሞ ወጣቶች ደም ትንሽ አንኳን አልከበደዉም ከነ አቦይ ስብሀት ጋር ቁርጥ ሲጎራረስ!!!አዉነት ግን ህዉሀትና እነ ዳዉድ ተጣልተዉ ነበር??አሁን አሁን ሳስበዉ ዳዉድ ኢብሳና አብረዉት ያሉት ጥቂት መሰሪዎች የዛ መሰሪ መለስ ዜናዊ ስትራቴጂዎችና እንደዚ ህዉሀት ለክፉ ቀኔ ይጠቅሙኛል ብሎ ያስቀመጣቸዉ ቅጥረኞች ይመስሉኛል ።
27 አመት ሙሉ ወያኔ ህዝባችንን ሲያርድ ሲገልና ሲደፍር 1 ቀን እንኳን መሳሪያ ተኩሶ የማያዉቀዉ ይሄ ሽማግሌ አሁን በሰላም እንዲገባ ሲፈቀድለት እንዲ መደንፋቱ በጣም ያመኛል!!ጭራሽ ብሎ ብሎ ከኛዉ የወጣዉን ህዉሀት በቦንብ ሳይቀር ሊያጠፉዉ የሞከረዉንና እንደሱ ኤርትራ ተደብቆ ምቾት እና መንደላቀቅ ሳያምረዉ ፊት ለፊት የተጋፈጠዉን አብይን ለማጥላላት መሞከሩ በጣም ያስገርማል!!ለማንኛዉም እኔ ያለሁበት አንቦና ሙሉ ኦሮሚያ ከአብይ ጎን ነዉ!!!ነቀምት አካባቢም የዳዉድ ሽፍቶች በመሳሪያ ህዙቡን እያስፈራሩት ስለሆነ ነዉ እንጂ ህዝቡ ተደምሯል!!ህዉሀትና ዳዉድ የሚቃወማቸዉ ወገናቸዉን እራሱ ከማጥፋት ወደ ኃላ የማይሉና በፓርቲ ስም ህዝብ ዉስጥ ለመደበቅ አየሞከሩ ያሉ ቆሻሾች ናቸዉ ቶሎ መንግስት ቅጣታቸዉን ሊሰጣቸዉ ይገባል!!!! ለዉጡን ያመጣዉ ጃዋርም አደለም ዳዉድም አደለም ማንም ግለሰብ አደለም ለዉጡን ያመጣዉ ሙሉ የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ ነው!!ማንም ሲፈቀድለት ከተደበቀበት ሀገር እየመጣ ለዉጡን ያመጣሁልህ እኔ ነኝ እኔን ነዉ መስማት ያለበት እያለ ቄሮና የኦሮሞን ህዝብ ማጃጃልና አንደ መሪ ማሽከርከር አይችልም!!እንደዚ የምትነዱትን ጅል ስትዝናኑ የነበረበት አሜሪካ ላይ ፈልጉ!!”።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.