መንታ መንገድ ክፍል 13

መንታ መንገድ
ክፍል አስራሶስት

.
.
ሀያት ከተመረቀች በኋላ ቤተሰቦቿም የሰርጉን ነገር
ቀድመዉ አናግረዉኝ ስለነበር የዝግጅቱ ጥድፊያ ዉስጥ
ገባን። አዳራሽ መከራየት ፣ ለጊዜዉ የምንኖርበት ቤት
መከራየት ፣ የቤት እቃ መገዛዛት ኧረ ስንቱ ተዘርዝሮ
ይቻላል? ጣጣዉ ብዙ ነዉ። ደስ የሚለዉ የቤት ዕቃ
መገዛዛቱን ኢስራዕ እና መርየም ከኢማን ጋር ሆነዉ
አገዙን። እኔ ቆንጆ ቤት አግኝቼ ተከራይቻለሁ። የእናቴን
ፀባይ ስለማዉቀዉ ከሀያት ጋር ብቻችንን እንድንኖር
ፈለግኩ እንጂ እናቴ ከሷ ጋር እንድኖር ጠይቃኝ ነበር።
ሰዒዶ የአዳራሹን ነገር ጨርሷል። የአክስቴ ልጆችም
በጣም አግዘዉኛል። በተለይ ኢማን የሷ ሰርግ ነበር
የሚመስለዉ። ብቻ ዋና ዋናዉን ጨርሰን የጥሪ ስራዎችን
ምናምን መስራት ጀመርን። የሰርግ ጣጣ ግን ብዙ ነዉ።
ከምር እንደዉም ቢቀር ያስብላል። ቀለል ያለ ድግስ
ቢሆን ይሻል ነበር።
.
ከብዙ ዉጥረት በኋላ የሰርጉ ቀን ደረሰ። ይገርማል አባዬ
ኒካህ ላይ ተገኝቶ ለሰርጉ ሳይደርስ ሞተ። አንደኛ ሚዜዬ
ሰዒድ ነዉ። ሁለተኛናሶስተኛ ሚዜዎቼ የአጎቴ ልጆች
ናቸዉ።
በሚዜዎቼ ታጅቤ ሀያትን በወጉ ከቤቷ ወሰድኳት። ሀዩ
ቬሎ አምሮባታል አይገልፀዉም። አዳራሹ ሰርጋችንን
ለማድመቅ በመጡ እድምተኞች ደምቋል። የሙሽራዉ ቦታ
ላይ ከሚዜዎቼ ጋር ተቀምጬ ሰውን አየሁት!
ይበላል፤ይጠጣል። በጣም ደስ አለኝ። በየአንዳንዷ ጉርሻ
ዉስጥ ሀያትን ላይመኝ ማጣቱንና የኔ መሆኗን አብሮ
የሚዉጥ መሰለኝ።
.
የሰርጉ ቀን ማታ ከሀዩዬ ጋር ሆቴል ነበር ያደርነዉ። ልክ
ክፍላችን እንደገባን ሁለታችንም ትንሽ ደከም ብሎን
ስለነበር ገላችንን ታጠብን። ትንሽ ቀለል አለን። እራት
በልተን ከጨረስን በኋላ ከሀዩ ጋር የፍቅር ጨዋታዉ
ተጀመረ። እየተሳሳምን ልብሷን ቀስ ብዬ አወለቅኩትና
በጡት ማስያዣናበፓንት ብቻ አስቀረኋት። ዉበቷ
ሊያቀልጠኝ ምንም አልቀረዉም። በጣም ታምራለች።
ገላዋ ዉብ ነዉ። ዛሬ ለኔ ብቻ የተገለጠ፣ ማንም ያላየዉ
ገላ! ልብሴን በዚህ ፍጥነት ማዉለቅ እንደምችል
እስከዚህች ቅፅበት ድረስ አላዉቅም ነበር። ሀዩ
እንደዛሬዋ ቀን የጓጓችለት ቀን ያለ አይመስለኝም።
አልጋዉ ላይ ተጋድመን መሳሳም ጀመርን። የተቀደሰ
መሳሳም! ትዳር ነዉና መልዓክት ሳይቀር በደስታ ሳይዘምሩ
አይቀሩም። ስሜቴ በጣም እየጋለ መጣ። እራሴን
መቆጣጠር ከበደኝ። ሳላስበዉ ሀዩን በጥፊ መታኋት እና
የጡት ማስያዣዋን ከሰዉነቷ ላይ ገንጥዬ አነሳሁት። ሀዩ
በጣም ደንግጣለች ግን ከስሬ ሁና የማደርገዉን ታያለች።
ለመነሳት አልሞከረችም። እዛዉ እንደተንጋለለች በጥፊዬ
ህመም ምክንያት ከአይኗ እንባ እየፈሰሳት የልቤን
አደረስኩ።
.
ሀያትን ምንም ስሜቷን ሳልጠብቅ ነበር የተገናኘኋት።
መረጋጋት ተሳነኝ። ስሜቴ ሲግል በጥፊ የመታኋት ለምን
እንደሆነ አላዉቅም። ግን ከዚህ በፊት ራሄልንም መትቼያት
ነበር። አሁን ትንሽ ግልፅ ሆነልኝ። አልጋ ላይ መረጋጋት
አልችልም። ሀዩን ማየት በጣም አፈርኩ። ተንደርድሬ ወደ
በረንዳዉ ወጣሁ። በረንዳዉ ላይ ያለዉ ዥዋዥዌ ወንበር
ላይ ተቀምጬ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። በምድር ላይ
ያለዉን የደስታ ጥግ ማጣጣም ካለመቻል በላይ ምንም
ህመም ሊኖር አይችልም። የሚስትን ክብር መጠበቅ
ካለመቻልናስሜቷን ለማስተናገድ ብቁ ካለመሆን በላይ
ከባድ መርዶ የለም። ጌታዬ ምነዉ ሀዘኔ በዛ?
.
አልቅሼ ስገባ ሀዩ አልጋዉ ዉስጥ ገብታ ተኝታ ነበር።
ፈገግ ለማለት ሞከረች። እየቀፈፈኝም ቢሆን ከአጠገቧ
ሄጄ ተኛሁ። ደረቴ ላይ ልጥፍ ብላ ተኛች። ደረቴ ላይ
ስትተኛ ብዙም እንዳልተከፋችብኝ በማሰብ በጣም ደስ
አለኝ።
.
በነጋታዉ ከሆቴል ወደ ተከራየነዉ ቤት ሄድን። ማታ ላይም
ስንደግመዉ ስሜቴ ሲግል እጄ ጥፊ መሰንዘሩንና መድፈር
በሚመስል መልኩ መገናኘቴን መተዉ አልቻልኩም።
ሳምንት ሙሉ አየነዉ ፣ ያዉ ነዉ።
በሳምንቱ የስነ ልቦና ባለሙያ አማከርኩኝ። የህይወት
ታሪኬን ሁሉ ከፈተሸ በኋላ ምናልባት የችግሩ መንስኤ
የእናትናአባቴን ድብድብ ሳይ ማደጌ ሊሆን እንደሚችል
ነገረኝ። የአባቴና የእናቴ ፀብ ለኔም ተረፈ? ታዲያ ለምን
ፀባዬ ግንኙነት ስፈፅም ብቻ ይቀየራል? መልስ
አላገኘሁለትም።
.
ሀያት ትምህርቷን እንደመጨረሷ በተማረችበት ሙያ
መስራት ትፈልጋለች። ዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ ዉጤት ስላላት
መምህር እንድትሆን ሊያስቀራት ፈልጎ የነበረ ቢሆንም
እሷ አልተቀበለችዉም። አሁን አዲስ ሆቴል ከአዲስአበባ
ዉጪ ለመክፈት አቅደናል። ሀጅራ እስክንድር እኔና ሀዩ
ተሰባስበን ከመከርንበት በኋላ ሆቴሉን ራሄል ልንለዉ
ወሰንን። ራሄልን የምናስታዉስበት አንድ ተቋም ይሆነናል
ብለን አስበናል። ለሆቴሉ ግንባታ የኛ ቤተሰብ እና የሀዩ
ቤተሰቦች በአክሲዮን መልክ ከፍተኛዉን መዋጮ አዋጣን።
መሬት የከተማዉ መዉጫ ላይ አገኘን። የህንፃዉም
የዲዛይን ስራ ተጀመረ።
.
ሀያትን በአግባቡ ልገናኛት አለመቻሌ እንደድሮዉ ፈታ ብዬ
እንዳላወራት አደረገኝ። የተገናኘኋት ጠዋት ሀፍረት
ሊዉጠኝ ይደርሳል። ምንም ሳላወራ ቁርሴን በልቼ ወደ
ስራ እሄዳለሁ። ሀያት ግን ስሜቴን ስለተረዳችዉ ፈታ
ልታደርገኝ ትሞክራለች። ጠዋት ወደ ስራ ስሄድ መኪናዬ
ከአይኗ ሳይርቅ ወደ ቤት አትገባም። ልብሴ ሆና
ሚስጥሬን ሸሽጋልኛለች።
.
አንድ ቀን ከሀያት ጋር የሀዩን ወላጆች ለመጠየቅ ወደ
ቤታቸዉ ሄድን። በልተን ፣ጠጥተን ከተጫወትን በኋላ
ልንሄድ ስንል የሀያት አባት ዱኣ ማድረግ ጀመሩ።
ሁላችንም አሚን እንላለን። ከዱአቸዉ በጣም ልቤን
የነካዉ ለሀያት ታናሽ እህት መግፊራ ያደረጉት ፀሎት
ነበር። “እንደ አክረም ያለ እንከን አልባ ባል ስጣት።” ነበር
ያሉት። ሀያትን አየኋት እሷም “አሚን” አለች። ስንት እንከን
እንዳለብኝ እያወቀች አሚን ማለቷ ገረመኝ። ሀዩ ጉድለቴን
እስከመች ትቆቋመዉ ይሆን? እየጎዳኋት እንደሆነ
እየተሰማኝ ነዉ። ሀፍረቴ ጣራ እየነካ ሲመጣ ሀያትን
እንድንፋታ ልጠይቃት ወሰንኩ። ከስራ እንደተመለስኩ
ጭኖቿ ላይ ተኝቼ ፀጉሬን እየደባበሰችኝ “ሀዩ እኔ ከዚህ
በላይ ባልጎዳሽ እና ባትሰቃዪ ደስ ይለኛል። ልፍታሽ?”
አልኳት።
ሀዩ በአጭሩ ምላሹን ሰጠችኝ። ግንባሬን ሳመችና “ከብዙ
ጥረት በኋላ ነዉ ያገኘሁህ። በግንኙነት ከሌላ ሰዉ ጋር
በእርካታ ከመኖር ከአንተ ጋር ዘላለም እንዲህ መኖሩን
እመርጣለሁ። እኔ እታገሳለሁ። አንተ ግን ደግመህ ይሄን
ጥያቄ እንዳትጠይቀኝ!” አለችኝ።
.
ከሀዩ ጋር አብረን መኖር ከጀመርን አምስት ወራት
ተቆጠሩ። ሀዩም አምስት ወር ሙሉ በጥፊ እየተመታች
ክብሯን ባልጠበቀ መልኩ ስገናኛት ችላኝ አለች። ያለፉትን
አምስት ወራት ለሊቱን ተነስቼ ጌታዬ መረጋጋትን
እንዲሰጠኝ ሳልጠይቀዉ ቀርቼ አላዉቅም። ሀዩን
ከተገናኘሁ በኋላ ወደ በረንዳ ሄጄ መንሰቅሰቁ የዘወትር
ተግባሬ ሆኗል። ገንፎዉ ተሰጥቶህ ማንኪያዉን ስትቀማ
በጣም ያሳዝናል!
.
ከሀያት ጋር ስተኛ የሚፈጠረዉን ነገር በተመለከተ ለማንም
አልተናገርኩም ነበር። የመጨረሻ አማራጬ ግን ለሰዒድ
ማማከር ነበር። እሱ መፍትሄ አያጣም።
ሰዒድን ለማማከር በወሰንኩ በነጋታዉ ሰዒድ ወደ ቢሮዬ
የማማክርህ ጉዳይ አለኝ ብሎኝ መጣ።
እንደተቀመጠ “ሰዉየዉ እንደዳርኩህ ልትድረኝ ነዉ!”
አለኝ።
“ሰዒድዬ በአላህ እኛ የቀመስነዉን ደስታ ልትቀምሰዉ
ነዉ?” አልኩ የተደሰትኩ ለመምሰል እየሞከርኩ። እኔ በሀዩ
ደስተኛ ብሆንም ሀዩን ግን እያስደሰትኩ አይደለም።
“ሊያዉም ልዛመድህ ነዋ!” አለኝ ፈገግ ብሎ
እያፈጠጠብኝ
“ማንን? መግፊራን? አላምንም!” አልኩት። መግፊራ
የሀያት እህት ናት።
“አይደለም ባንተ በኩል። አክስቶችህ ሰፈር!” አለኝ።
ሁለታችን
ም አይን ለአይን ተያይተ

ን ሳቅንና እኩል “ኢማን” አልን።
ኢማን ሁሌም እኛ ቤት መጥታ እሱ ካለ እኔን ደክሞሀል
ምናምን ብሎ ሰበብ ሰጥቶ እሱ ነበር ወደ ቤቷ
የሚያደርሳት።
“እና አዉርታችኋላ!” አልኩት።
“ሁሉም አልቋል። ኒካህ ብቻ!” አለኝ እየሳቀ። ኢማን
በጣም የምወዳት የአክስቴ ልጅ ናት። በፀባዩ
የምተማመንበትን ጓደኛዬን ስለምታገባ ደስ አለኝ። የሱን
ጉዳይ አዉርተን እንደጨረስን የእኔን ጉዳይ በሙሉ
ነገርኩት። ሰዒድ ለኔ በጣም አዘነና “አክረሜ ይሄ ነገር
ድግምት ሊሆን ይችላል። ብዙ ሴቶች ይወዱህ ስለነበር
አስነክተዉህ ይሆናል።” አለኝ። ወደዱኝ ከተባሉት ሴቶች
የቀረብኳቸዉ ሀያትንእናራሄልን ነዉ። ሁለቱም ደግሞ እኔን
የሚጎዳ ነገር እንደማያደርጉ እርግጠኛ ነኝ። ቢሆንም
ነገሮችን ማረጋገጡ ሳይሻል አይቀርም በሚለዉ በቁርዓን
ህክምና ጤናዬን ልንፈትሸዉ ወሰንን።
.
በነጋታዉ ለማንም ሳንናገር እኔናሰዒዶ ወደ አንድ የቁርዓን
ህክምና ማዕከል ሄድን። ብዙ ሰዉ ከኔዉ ጋር በተያያዘ
ጉዳይ ማለትም በድግምት እና በአጋንንት ተበጥብጦ
ህክምና ለማግኘት ተቀምጧል። በመሀል ከተማችን
ዉስጥ እንደዚህ ድግምት አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ አሳዘነኝ።
ተራዬ ሲደርስ ወደ ህክምና ክፍሉ ገባሁ። ሰዒድም
አብሮኝ ገባ። አንድ ነጭ ጀለቢያ የለበሰ ኡስታዝ
ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ ችግሬን ካዳመጠኝ በኋላ
ወደ ቀጣዩ ክፍል አስገባኝ። ቀጣዩ ክፍል ሙሉ ለሙሉ
ምንጣፍ የተነጠፈበት ክፍል ነበር። የመኪናዬን ቁልፍ
እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የያዝኳቸዉን ነገሮች ለሰዒድ
ከሰጠሁት በኋላ ሰዉየዉ ጮክ ብሎ ቁርዓን መቅራት
ጀመረ። መጀመሪያ ድምፁ በጣም ያምር ነበር። ከዛም
የሆነ ብስጭት ዉርር አደረገኝናድምፁ አስጠላኝ። ከዚህ
በኋላ ምን እንደተፈጠረ ነቅቼ ሰዒድ እስኪነግረኝ ድረስ
አላዉቅም።
.
ይጥላል:”'””

3 thoughts on “መንታ መንገድ ክፍል 13

  1. Betam wedenewal dess yelale gen 1 kefel beca yansale 😔😔 2 betaregut dess ☺☺☺☺yelenale

    1. እናመሰግናለን! ያው እየተጠናቀቀ ስለሆነ በአዲሱ ላይ እንደዛ እናረጋለን

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.