መንታ መንገድ ክፍል 14

መንታ መንገድ
ክፍል አስራአራት

.
.
ራሴን ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ አላዉቅም ነበር።
አይኔን ስገልጥ ነጭ አምፖል ሰማያዊ ኮርኒስ ላይ
ይታየኛል። ወዲያዉ ቀና ስል ከፊት ለፊቴ ሰዒድ እና
ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉዬ እየተመለከቱኝ ነበር።
ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉ ወዲያዉ ጌታዬን
እንዳመሰግን አዘዘኝ። አመሰገንኩ። ወዲያዉ ወደ ጆሮዬ
ተጠግቶ ለስግደት ጥሪ የሚደረገዉን አዛን እያደረገ
የማጅራቴን ደምስሮች በጣቱ ነካካቸዉ።
“ሴቶች በጣም ይወዱህ ነበር?” አለኝ ኡስታዙ ሰዒድ
አጠገብ እየተቀመጠ
“እንደዛ ነገር” አልኩት።
“ያይኔአበባ የምትባል ሴት ታዉቃለህ?” አለኝ አይን አይኔን
እያየ።
“አዎ ዩኒቨርሲቲ ስማር የምጠቀምበት ምግብ ቤት
አስተናጋጅ ናት።” አልኩት።
ሰዒድ በግርምት አንገቱን ነቀነቀ። ኡስታዙ “እዛ ቤት
በጣም ጣፍጦህ የበላህበት ቀን ትዝ ይልሀል?” አለኝ።
እንደድንገት አንድ ቀን የበዓል ስጦታ ብላ ያይኔአበባ
የሰጠችኝ ምግብ ትዝ አለኝ። እንደዉም ብቻዬን ዶርም
ነበር የበላሁት። ኡስታዙ ሌሎች ጥያቄዎችንም ጠይቆኝ
ከመለስኩለት በኋላ ድግምቱ የተሰራብኝ በያይኔአበባ
እንደሆነ ነገረኝ። ያይኔአበባ ወዳኝ እንደነበር ግን
ልትፎካከራቸዉ በማትችላቸዉ ቆንጆ ሴቶች ተከብቤ
የነበረ በመሆኑ ድግምት እንዳሰራችብኝ ራሴን በሳትኩበት
ሰዓት ዉስጤ የነበረዉ ጋኔን መናገሩን አረዱኝ። ኡስታዙ
አሁን በፈጣሪ ፈቃድ ድግምቱ መክሸፉንና ዉስጤ
የነበረዉ መጥፎ ስሜትም እንደሚወገድ አበሰረኝ።
በሀይማኖቴ መጠንከር እንደሚኖርብኝ መክሮ ከግብረስጋ
ግንኙነት በፊት ላደርጋቸዉ የሚገቡ ነገሮችን መከረኝ። .
በተፈጠረዉ ነገር እኔም ሰዒድም ተገርመናል። መኪና
ዉስጥ እንደገባን ሰዒድ “በል እስኪ ዛሬ ሂድና ሞክራት
እና ጉዱን እንየዉ!” አለኝ እየሳቀ። እዉነት ለመናገር
በጣም ቅልል ብሎኛል።
.
ማታ ቤት ስገባ ሀዩ አኩርፋ መጅሊሱ ላይ ተቀምጣለች።
ደሞ ምን ተፈጠረ? “ሀዩዬ ምን ተፈጠረ?” አልኳት ከጎኗ
እየተንበረከክኩ።
“አክረሜ ልዉለድልህ ፍቀድልኝ!” አለች እያለቀሰች።
የአልጋ ላይ ፀባዬ እስኪስተካከል ላለመዉለድ ወስኜ
መድሀኒት እንድትወስድ አዝዣት ነበር። አይ ሀዩ! ከነዚህ
የአልጋ ላይ ፀባዬ ምንም ሳትጠላኝ ልትወልድልኝ መጓጓቷ
የፈጣሪ ስጦታ እንደሆነች እንዳስብ አደረገኝ። ፈገግ
አልኩና “አላህ ካለ ነገ ጠዋት መልሴን እነግርሻለሁ!”
አልኳት ዛሬ ማታ ሊፈጠር የሚችለዉን ሰላማዊ ለሊት
ተስፋ እያደረግኩኝ።
.
ማታዉን ኡስታዙ በነገረኝ መልኩ ግንኙነት ከመፈፀማችን
በፊት ሰግጄ ፀሎት አደረስኩ። ከዛም የሀዩ ጭንቅላት ላይ
መዳፌን አስቀምጬ ጌታዬን ለመንኩ። ዉስጤ በእርጋታ
ተሞልቷል።
ሀዩን ሳምኳት ፣ እጄ ጥፊ እንዳይቀድመዉ ፈርቼያለሁ።
እየተሳሳምን በስሜት ጠፋን። እጆቼ ሰዉነቷ ላይ
ተንሸራሸሩ። ልክ እንደሰዉ ተገናኘኋት። ሀዩ ፊቷ በእርካታ
ተሞልቶ እየሳቀች “ጌታዬ እንደማያሳፍረኝ አዉቅ ነበር።”
አለችኝ። የረዥም ጊዜ ፀሎቷ ይሄ ነበር መሰለኝ።
ሁለታችንም መድገም ፈለግን! ሀይል አሰባስበን
ደገምነዉ። እርካታ ጣራ ነካ! ማመን ከበደኝ። የምድርን
ጣፋጩን ነገር በእርጋታ ማጣጣም ቻልኩኝ። ሀዩ እቅፌ
ዉስጥ ቀለጠች። ፍልቅልቅ እያለች “አፈቅርሀለሁ።”
አለችኝ። ጌታዬን አመስግኜ ሀዩን እቅፍ አድርጌ ተኛሁ።
.
በነጋታዉ ጠዋት ሀዩ ከእንቅልፍ እንደተነሳን የወሰደችዉ
የመጀመሪያዉ እርምጃ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖችን
መጣል ነበር። አሁን ልጅ ያስፈልገናል። ጠዋቱን ሰዒዶ
ደወለና “እ ጄኪጃን አደብ ገዝተህ አደርክ ወይስ?” አለኝ።
“ኧረ አልሀምዱሊላህ ዛሬ ጥፍጥናን አጣጣምኩት። አሁን
ከልቤ እንድትቀምሰዉ ተመኝቼልሀለሁ።” አልኩ

One thought on “መንታ መንገድ ክፍል 14

  1. It’s an amazing story while I was reading this writing it self was so alive and vivid I felt how they where feeling.its also a great satisfaction of work well done. When we look at it spiritually is showed as that prayer works we need to pray for everything it will be answered.

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.