ሕይወቴ ክፍል 6

#ሕይወቴ•••

#ክፍል_6

እኔና ሄኖክ ልብሳችንን ቀያይረን ስራ ወደተገኘበት ቦታ ሄድን,ወይ ስራ ይገርማል …..ለማንኛውም ከመቀመጥ ይሻላል ,ያገኘልኝ ስራ ግሮሰሪ ውስጥ ብርጭቆ ማጠብ ነበር ,ይሄንን ስራ የመረጠው ማታ የሚያመሸው እዛ ስለሆነ ስራ ስጨርስ ወደ ቤት ይዞኝ እንዲሄድ በማሰብ ነበር በዛውም የግሮሰሪው ባለቤት ጋደኛው ነው, ግሮሰሪው ቺቺኒያ አካባቢ ነው ስራ ቦታው ስንደርስ አጋጣሚ አሰሪው አልነበረም ነይ ብሎኝ በረንዳ ላይ ቁጭ አልን ,;
-,
የሚገርመው እዛ ቁጭ ብለን ሄኖክን እየመጡ ሰላም የሚሉት ሰዎች አበዛዛቸው ሴቶቹ ወንዶቹ ይገርማል ደግሞ እርግማን ብለው ነው የሚጠሩት እኔማ በቃ እርግማን ልለው ወሰንኩ ሆይ ይሄን ያክል ስሙ ተወዳጅ ከሆነ ,;
-,
የሴቶቹ ብዛት አንዷ የለበሰችው ልብስ ብታዩዋት ባትለብስ ይሻላል እራቆቷን ነች ብቻ ምን ልበላችሁ የቀለም ፋብሪካ ትመሰላለች ተለቅልቃ ተለቅልቃ በዛላይ ይሄንን የፈረስ ጭራ የመሰለ ዊግ ተሽክማዋለች ብቻ ምን እንደምትመስል ,ድንገት .ደመቁ?ነይ አላት እርግማን ድንግጥ አልኩ እሷም እእ !!እርግማን አለችና የተጫማችው ጫማ ትልቀቱ አይጣል ነው እየተወላገደች መጣች ሰላም ነው አለች እየተሞላቀቀች ,ሰላም አለችን እህቴ ናት አትሞላቀቂባት አላት OMG እንዴት ውብ የሆነች እህት አለችህ ሜሮን እባላለው አለችኝ እጇን ዘርግታ ሳራ እባላለው ብዬ ተዋወቅኃት ;ግራ እንደገባኝ አውቃ እርግማን ግን ደመቁ ማለትህን አታቆምም አለችው ;እኔም ቅፅል ስምሽ ነው አልኩ , ሳርዬ ግራ ገባሽ አይደል አለኝ እርግማን ምን መሰለሽ ከገጠር ክልል ይመጡና ልክ ከተማ ሲገብ ሜሪ ሊሊ እያሉ ይሞላቀቃሉ ትክክለኛ ስማቸው ደመቁ በቀሉ ከበብሽ ነው ብሎ ሀሀሀሀ እያለ ሳቀ,; እኔንም አሳቀኝ በሉ ቻው ወሬ አለብህ ብላው ሄደች.
‘,
ትንሽ እንደቆየን ዝንጥ ብላ የለበሰች ውብ የሆነች ልጅ መጣች ,አትጠገብ ነይ አላት አሁንም ወይኔ ጉዴ ግራ ገባኝ ሰላም ነው ሄኖክ አለችው እኔንም ሰላም አለችኝ ስረአት ያላት ትመሰላለች በዛላይም ውብ ናት ስሟ መክሊት ይባላል ብቻ ብዙ ሴቶችን አየሁ ሁሉም እርግማንን ያውቁታል ,;ሆኖክ አልኩት ወዬ ሳሪ አለኝ ምንድናቸው ግን አልኩት ግራ ገባሽ አይደል አለኝ እ!አልኩት እዚህ ጋ ትንሽ ገባ ብሎ ጭፈራ ቤት አለ እዛ ነው የሚሰሩት የሌሊት ስራ ልክ አባቴ እቤት እንዳመጣት ሴት አይነት አለኝ ;,እጄን ተፀየፍኩት ስራቸውን አጣጥለው ሲያወሩ በቃ እጠላቸዋለው ,እጄን ልብሴ ላይ ሞዥቅሁት ,በዛ ቅፅበት አሰሪው ሰውዬ መጣ ወይ ግልግል አልኩ,;
-,
ሄኖኬ እንዴት ነህ አለው ሰላም ተባባሉ እህቴ ናት ተዋወቃት አለው ቶማስ እባላለው አለኝ ሳራ እባላለው አልኩት ,ስራ መጀመር እንደምችል ነገረኝ ደሞዝ 200 ብር እከፍልሻለው ቀስ እያልኩም እጨምርልሻለው አለኝ እኔ ብሩ መች አሳሰበኝ ከቤት ወጥቼ መግባቴ ለኔ ትልቅ ነገር ነው ዛሬ በዚች ቅፅበት ስንቱን ታዘብኩ ለካ እቤት መቀመጥ መታሰር ነው ነገ ስራ ልጅምር ነው ግልግል ጠዋት 5:00 ሰአት ገብቼ ማታ ከሄኖክ ጋር ወደ ቤት ሲገባ መሄድ እንደምችል ነገረኝ እሽ ብዬ ነገ ስራ እንደምጀምር ተነጋግረን እኔና ሄኖክ ተያይዘን ወደ ቤት ሄድን
-,
ከሄኖክ ጋር ገብያ ውስጥ ገብተን ከቀናት በኃላ ለምናከብረው ለእናታችን 2ተኛ ሞት አመት የሚያስፈልጉንን ገዝተን ደስ እያለኝ ወደ ቤት ሄድን ቀኑ ላይን ያዝ አድርጓል እቤት ስንደርስ ግን አባቴ እቤት ነበር የት ነበራችሁ አለ ገና በሩን ከፍተን ስንገባ ባቢ ሰላም አመሽህ ደስ አይልም ባቢ ስራ አገኝው አልኩት የምን ስራ አለኝ ሄኖክ አባቴን ሰላም ሳይለው የያዘውን እቃ ኩሽና አስቀምጦ ወደ ክፍሉ ገባ,; እኔም የያዝኩትን ዕቃ ኩሽና አስቀምጬ አባቢ ምን መሰለህ ከምቀመጥ ብዬ ነው ግሮሰሪ ውስጥ ነው ብርጭቆ ማጠብ አልኩት ምን ብሎ ጮኽ,

,,,,part 7 ይቀጥላል✍

ሕይወቴ ክፍል 5

#ሕይወቴ

#ክፍል_5

-,አባቴ ከመጠን በላይ ሰክሮ ቢሆንም መጣ ,ግን የሄኖክ ማምሽት ጨንቆኛል ግራም ገብቶቻል ,ድንገት ግን የቤታችን ስልክ ጮኽ ድነገጥኩ ምክንያቱም በዚህ ሰአት እኛ ቤት ስልክ አይደውልም እንኳን በዚህ ምሽት በቀንም ሳይደወል ሳምንት የሚቆይበት ጊዜ አለ, ቀስ ብዬ ስልኩን ተጠጋሁ እየተንቀጠቀጥኩ ስልኩን አነሳሁት ,;ጎርነን ያለ ድምፅ “ሀሎ! አለኝ …………,በሚንቀጠቀጥ ትንፍሽ “ሄሌ !አልኩት ይቅርታ በዚህ ምሽት ስለረበሽኩ የሄኖክ ቤት ነው ? አለኝ በዛ በሚያስፈራ ድምፅ ,አወ ምነው ችግር አለ? ወንድሜ ምን ሆነ ? ምን ተፈጠረ አልኩት? አይ ከሰው ጋር ተደባድቦ ፓሊስ ጣቢያ ነው ያለው እኔም ከዛ ነው የምደውለው ,ሳጅን ክበበው እባላለው,ሲለኝ ውሀ ሆንኩ. ምነው እሱ ግን ደህና ነው? የደበደበውስ ስው ተጎድቷል ? እሽ መቼ ልምጣ ?አልኩት ተረጋጊ ሄኖክ ደህና ነው ነገ ጠዋት መምጣት ትችያለሽ እዚህ መሆኑን እናሳውቃችሁ ብለን ነው አለኝ,እሽ አመስግናለው ብዬው ስልኩ ተዘጋ,;
-,ተንደርድሬ ወደ አባቴ ሄድኩ ባቢ አልኩት ? በዚች ትንሽ ደቂቃ ውስጥ እልም ያለ እንቅልፍ ወስዶታል ከነ ልብሱ ከነ ጫማው ነው ዝም ብሎ በደረቱ የተኛው ,ብጠራውም አልስማም አለኝ ,እንባዬ በጉንጮቼ ሲፈስ እያለቀስኩ መሆኑ ታወቀኝ ;,አንድ ወንድሜ ነው እወደዋለው በጣም. ክፉውን መስማት አልፈልግም ,ሶፋው ላይ ሄጄ በቁሜ ወደቅሁበት,ምንድነው የማደርገው ብዬ ብዙ አሰብኩ ጠዋት አባቴ ከመውጣቱ በፊት ማነናገር እንዳለብኝ ወሰንኩ ስለዚህ ግዴታ እዚሁ ሶፋ ላይ መታኛት ነው ያለብኝ ሲወጣ እንድሰማው ብየ እዛው ተኛሁኝ;,
-,መንጋት አይቀር ነጋ አባቴ የመኝታ ክፍሉን ሲከፍት ነው ብንን ያልኩት ,ደህና አደርሽ ልጄ ይቅርታ ቀሰቀስኩሽ ግን ለምን እዚህ ተኛሽ አለኝ……. ብድግ ብዬ ደህና አደርክ ባቢ ,;ባቢ ባቢ ሄኖክ ታስሯል ማታ ስልክ ተደውሎልኝ ነበር መጥቼ ስቀሰቅስህ አልሰማም አልከኝ አልኩት…. ደነገጠ መቼ የት ለምን ብሎ ጠየቀኝ ;ሁሉንም ነገር ነገርኩት ,ለሄኖክ መታሰር ብርቁ አይደለም ሁሌ ይታሰራል አድሮ ግን አያውቅም , አባቴ ቶሎ ያስፈታው ነበር ,ዛሬ ግን አደረ , አባቴም በቃ ልሂድ ቻው አለኝ እሽ ባቢ ግን ደውሉልኝ እሺ ,አልኩት እሺ ብሎኝ እየበረረ ሄደ ,; እኔም ቶሎ ብዬ ኩሽና ገባሁ ሄኖክ እርቦት ስለሚመጣ እንደመጣ ምግብ መብላት አለበት ቶሎ ብዬ ቁርስ አዘጋጀሁለትና መምጫውን መጠባበቅ ጀመርኩ, ብዙም ሳይቆዬ,, .አባቴና ሄኖክ ተያይዘው መጡ የሚገርመው አስፈትቶትም አይነጋገሩም ልክ በሩን ከፍተው ሲገብ ተንደርድሬ ተጠመጠምኩበት ይቅርታ እህቴ አስጨነቅሁሽ አይደል አለኝ ደህና ነህ አልኩት ደህና ነኝ አለኝ ቁርስ ትበላለህ ስለው ሻወር ልውስድና እሽ ብሎኝ ወደ ክፍሉ ገባ አባቴን አመስግናለው ብዬ አቀፍኩት ችግር የለውም በቃ እኔ ወደ ስራ ልሂድ ብሎኝ ሄደ,,,,
በነገራችን ላይ ሄኖክ ከትላንት ወዲያ አባቴ ይዟት የመጣችውን ልጅ ሊያናግራትና ሁለተኛ ከአባቴ ጋር እንዳትመጣ ሊያስጠነቅቃት ሄዶ ነው ከሷ ጋር የነበረው ወንድ እኔ እያለው እንዴት ላናግርሽ ትላለህ በማለት ተጣልተው ነበረ የደበደበው ,;ደግነቱ ብዙም አልተጎዳም ለዛ ነው ቶሎ የለቀቁት ቢጎዳማ ኖሮ እዛው ይከርም ነበር ።ሄኖክ ሻወር ወስዶ ወጣ ቁርስም በላ በቃ ዛሬ አልወጣም ልተኛ ስራ አግንቼልሻለው ከሰአት አብረን ሄደን እናናግራቸዋለን አለኝ እሽ አልኩት እሱም ተኛ እኔም ስራዬን ተያያዝኩት ምሳ ሰራሁ ቤት አስተካከልኩ ልብስ አጠብኩ ከዛ ሄኖክን ቀሰቀስኩትና ምሳ በላን ልብስ ቀይሬ እሱም ቀይሮ ተያይዘን ወጣን ስራ የምቀጠርበት ቦታ ደረስኩ….. ወይ የስራው አይነት ይገርማል ,,,,,,,

ይቀጥላል

መንታ መንገድ ክፍል 15 የመጨረሻው ክፍል

እናመሰግናለን።
መንታ መንገድ
ክፍል አስራአምስት

.
.
ሀዩዬ እንደሷ ቆንጆ ልጅ ወልዳልኝ ሆስፒታል ከተኛች
በኋላ በሀኪሞቹ ፈቃድ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ወሰድናት።
እናቷ ሁሉንም ነገር አዘጋጅተዉ ጨርሰዉ ነበር። ገንፎ
ለሀዩ ይሰራል መግፊ በሷ እያሳበበች ትበላለች።
የኔናየመግፊ የሰሞኑ ትርርባችን በገንፎዉ ጉዳይ ላይ
ነዉ። ፓምፐርስ ምናምን ከመግፊ ጋር ሆነን ገዝተናል።
መግፊ ሆነ ብላ ሴሪፋም አስገዝታ መሳቂያ አደረገችኝ።
ለካ እስከ ስድስት ወር ከጡት ሌላ ምንም አይነት ምግብ
ለህፃናት አይሰጥም።
ሀዩዬን ልጃችንን ስታጠባ አየኋት ፤ የሆነ ልብ የሚይዝ
ነገር አለዉ። ልጇን ስትንከባከብ በጣም ደስ ትላለች።
.
በሰባተኛዉ ቀን ሁለት በግ አርደን ሰደቃ አወጣን። ሰደቃ
ማለት ምፅዋት ማለት ነዉ። በሀይማኖታችን መሰረት ልጅ
በተወለደ በሰባተኛዉ ቀን የሚደረገዉ ይህ የምፅዋት
ዝግጅት አቂቃ ይባላል። በነገራችን ላይ ለልጃችን ስም
ለማዉጣት በጣም ብዙ ክርክር ነበር የተፈጠረዉ።
መጀመሪያ ራሄል እንድትባል ፈልጌ ነበር። ግን የሀዩም
የኔም ቤተሰቦች በራስ ላይ ሀዘንን ማባባስ አያስፈልግም
ብለዉ ተቆጡኝና ተዉኩት። እንደዉም የሀዩ እናት
“ለሀያትም ስሜት አስብ እንጂ! ማትፈልጋት
እንዳይመስላት!” ነበር ያሉኝ። ሀዩ ብዙ ነገር ስላደረገችልኝ
ስሜቷን መጠበቅ ይኖርብኛል። ራሄልን ለመዘከር ሆቴሉ
ይበቃል። ብዙ የስም ምርጫዎች ከቀረቡ በኋላ መጨረሻ
ላይ “ራህማ” የሚለዉ የኔ ምርጫ ተቀባይነት አገኘ። እኔ
ራህማ እንድትባል የፈለግኩት ከራሄል ሞት በኋላ
የነበርኩበትን መጥፎ ሁኔታ ፣ አልጋ ላይ የነበረብኝን
ያለመረጋጋት ችግር እና ጥፊዬን ችላ ለኖረችዉ ዉዷ
ሚስቴ ሀያት ስጦታ እንዲሆን በማሰብ ነዉ። ነብዩ አዩብ
(እዮብ) በሽታ ሲፈራረቅበት ፣ ሀብቱ ሁሉ ሲወድም እና
ሌሎች ሚስቶቹ ትተዉት ሲሄዱ በፅናት ከጎኑ የቆየችዉ
አንዷ ሚስቱ ራህማ ብቻ ነበረች። እናም የኔ ልጅ ከብዙ
ችግር በኋላ የተገኘች ናትና የሚስቴን ትዕግስት ለመዘከር
ራህማ አልኳት። ራህማ ማለት እዝነት ማለት ነዉ።
.
ሀጅራ ፣ እስክንድር እና የሪቾ ቤተሰቦች ፤ ቤት መጥተዉ
ሀዩን አራስ ጠይቀዋታል። በነገራችን ላይ ሀጅራ
ታጭታለች። በቅርቡ ማግባቷ አይቀርም። የአክስቴ ልጅ
እና የዉዱ ጓደኛዬ ሰዒድ ሚስት ኢማን ሰሞኑን ከነሀያት
ቤተሰቦች ቤት ጠፍታ አታዉቅም። ኢስራዕ እና መርየም
ቤታቸዉ አድርገዉታል። ከመግፊራ ጋር ሆነዉ ሀዩን
ያዳብሯታል። እናቴም ከአባቴ ሞት በኋላ ትንሽ ስርዓት
ይዛለች። ከአክስቶቼም ጋር ታርቀዋል። ምግብ እየሰራች
ለሀዩ ይዛላት ትመጣለች። ከምር ልጅ ግን የደስታ ምንጭ
ነዉ። ስራ ዉዬ ማታ አይኗን እስከማይ እንዴት እንደምጓጓ!
በርግጥ ለሀዩዬ ያለኝም ፍቅር በጣም ጨምሯል።
.
ጊዜዉ በሀዩ ፍቅርና በራህማ ጨዋታ ታጅቦ ነጎደ።
ራህማዬ ሁለት አመት ሞላት። የራሄል ሆቴል ግንባታም
ተጠናቀቀ። አጠቃላይ እቃዎቹን ሳይጨምር ለግንባታ ብቻ
አስር ሚሊየን ብር አዉጥተናል። በርግጥ ቢዝነሱ
አስተማማኝ ስለሆነ በአመት ዉስጥ ይመልሰዋል። በዛ
ላይ ሀዩን የመሰለች የምርጥ ጭንቅላት ባለቤት ናት
የምታስተዳድረዉ። የዉስጥ እቃዎቹን ከዉጭ
ካስመጣንናእነሀያት ሰራተኞችን ከቀጠሩ በኋላ
የሚመረቅበት ቀን ደረሰ። ሆቴሉ በአክሲዮን የተከፈተ
ነዉ። የእኔ ቤተሰብ ፣ የሀያት ቤተሰብ ፣ የራሄል ቤተሰቦች
፣ እስክንድር ፣ ሰዒድ እና ሀጅራ ነን ባለድርሻዎቹ። ትልቁ
ድርሻ ግን የኔ እና የሀዩ ቤተሰቦች ነዉ። የሆቴሉ የቦርድ
ሰብሳቢ እኔ እንድሆን ተወስኗል። ሆቴሉን በስራ
አስኪያጅነት ደግሞ ሀያት ትመራዋለች። ምክትል ስራ
አስኪያጁ ልምድ ያለዉ ሰዉ ነዉ። ሀጅራ እና እስክንድርም
ዉስጥ ላይ የሀላፊነት ቦታዎችን ይዘዉ ይመራሉ።
ከምርቃቱ በፊት የማስታወቂያ ክፍላችን ሆቴላችን
በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ እንዲተዋወቅ አደረገ። እነሀያት
በስራዉ በጣም ተወጥረዋል። እኔ እንኳ የራሴን ስራ
ስለምሰራ በሳምንት አንዴ ነዉ ሪፖርታቸዉን ለማዳመጥ
የምሄደዉ።
.
ጠዋት ቢሮ ስገባ ፀሀፊዬ ሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ ስላሉ
እቃዎች ካወራችኝ በኋላ አንድ ደብዳቤ ሰጥታኝ ወጣች።
ከራሄል ሆቴል ይላል። እነሀያት እንደላኩት ገመትኩ። ከፍቼ
አነበብኩት።
“የራሄል ሆቴል የምርቃት ስነ ስርዓት በቀጣዩ ሳምንት
እንደሚደረግ ይታወቃል። በመሆኑም ሆቴሉ የራሄል
መታሰቢያ እንደመሆኑ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ስለ ራሄል
የሚዳስስ አጭር ፅሁፍ መቅረብ ይኖርበታል። ስለሆነም
እንደ ሆቴሉ የቦርድ ሰብሳቢነትዎ በእለቱ ይህን ሀሳብ
ባካተተ መልኩ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉልን
በአክብሮት እንጠይቃለን። ከሰላምታ ጋር!” ይላል። ከስሩ
የሀያት ፊርማ አለዉ። ረዥም ሰዓት ብቻዬን ሳቅኩ። ለምን
ሳቅኩ? ሀዩ ለኔ ደብዳቤ መፃፏ ገርሞኝ! እሷ ስራ ላይ
ቀልድ አታዉቅም።
.
የሆቴሉ ምርቃት ሲጠጋ ሀያት ስራ ስለበዛባት አንዳንዴ
አስፈቅዳኝ እዛዉ ታድራለች። ራህማን ሁሌም ስራ ስትሄድ
ይዛት ነዉ የምትሄደዉ። “አንተ እኔን እንጂ እሷን ማቀፍ
አትችልበትም!” ትላለች ሀዩ። ለነገሩ ራህማ መራመድ እና
ትንሽ ትንሽ መናገር ጀምራለች።
ከብዙ ዉጥረት በኋላ የራሄል ሆቴል ምርቃት ደረሰ። የዛን
ቀን ሀዩ ሆቴል ስለነበር ያደረችዉ ከኢስራዕናማማ ጋር
ሄድኩ። መርየም ከባሏ ጋር ሄዳለች። የሆቴላችን በር ላይ
ስደርስ ድባቡ ለየት ያለ ነዉ። መኪናዬን የሆቴሉ ፓርኪንግ
ጋር አቁመን ወደ ዉስጥ ገባን። ሱፍ የለበሱ ወጣቶች
ወዲያዉ እየተቀላጠፉ ወደ ሆቴሉ አዳራሽ ይዘዉን ሄዱ።
ብዙ ሰዉ አለ። አዳራሹ ጋር ስንደርስ ሀዩ በሩ ጋር ቆማ
እንግዳ እየተቀበለች አገኘኋት። ሰላም ካለችን በኋላ
ኮሌታዬን አስተካክላልኝ ወደ ተዘጋጀልን መቀመጫ
ወሰደችን። እንግዳዉ ሁሉ ቦታ ቦታ ከያዘ በኋላ መድረክ
መሪዉ ወደ መድረክ ወጥቶ የእለቱን ዝግጅቶች
አስተዋወቀ። ከዚያም ሀያትን ወደ መድረክ ጠርቶ እኔን
ንግግር እንዳደርግ እንድትጋብዘኝ አደረገ። እንግዲህ
የቦርድ ሰብሳቢዉ በስራአስኪያጇ መጋበዙ ነዉ። ሀዩ
ስታወራ አንቱ እያለችኝ ነበር። እኔ ሳቄን ለመቆጣጠር
እየታገልኩ ነዉ።
.
መድረኩ ላይ ወጥቼ ንግግሬን ጀመርኩ። ሁሉም አፉን
ከፍቶ ያዳምጣል።
“ዛሬ በዋናነት በስራ አስፈፃሚዎቻችን ብርታት ሆቴላችንን
ለመመረቅ በቅተናል። ግን መረሳት የሌለበት፤ ሆቴሉ
ትናንት አብራን በአንድ ጎዳና ላይ ስትጓዝ የነበረችናብዙ
ህልም የነበራት ጓደኛችን መታሰቢያ መሆኑ ነዉ። የራሄል
ዉበት በሆቴላችን አይነግቡነት ይገለፃል። የሰላ ብዕሯን
የማስታወቂያ ቡድናችን ተቋማችንን ያስተዋዉቅበታል።
ለሰዉ የነበራትን ፍቅር ሰራተኞቻችን እርስ በእርስ
ይዋደዱበታል። እሷን መልሰን ማግኘት ባንችልም ሆቴሉን
ትልቅ ደረጃ በማድረስ ከፍ አድርገን እንዘክራታለን። ራሄል
ሆቴል በይፋ ተከፍቷል!!” አልኩና ከመድረኩ ወረድኩ።
ታዳሚዉ ያጨበጭባል።
.
የመንግስት ባለስልጣናት ዲስኩራቸዉን ካሰሙ በኋላ
ታዳሚዉ ሆቴሉን እንዲጎበኘዉ ተደረገ። በየኮሪደሩ ላይ
የራሄል ፎቶ በሚያምር ፍሬም ተሰቅሏል። አንድ ጥግ ላይ
ደግሞ የራሄል የተመረጡ ግጥሞች በልዩ ዲዛይን
ተሰርተዉ ግድግዳዉ ላይ ተሰቅለዋል። አይኔ አንዱ
ግጥም ላይ አረፈ። መንታ መንገድ ይላል አርዕስቱ
“መንታ መንገድ ፊት ቆሞ ፈራጁ፣
ምረጥ ተባለ ከመንገዶቹ፣
ግራዉን መንገድ እየወደደዉ
ለሀይማኖት ሲል ቀኙን መረጠዉ።
ቀኝ በጎ ነዉ ሲባል የሰማ፣
ነገዉን ብሎ ግራዉን ያማ፣
ሚስኪን አፍቃሪ ፍቅሩን ተቀማ።
ግራዉ ፈራጁን ማግኘት ቢነፈግ፣
ፈገግታ ሰጡት ለቅሶ ሚሸሽግ።
ሳቀ ሳቀና አንብቶ አንብቶ፣
ፈራጅን ሲያልም ዉሎ አምሽቶ፣
ተስፋ ሲቆርጥ ፣ ፈርሶ አደረ፣
ከተጠራበት ፣ ከህ

ይወት ቀረ።”
ይሄ ግጥም ራሄል ተስፋዋ ሙጥጥ ሲልናራሷን ልታጠፋ
በወሰነችበት ቅፅበት የፃፈችዉ እንደሆነ ገመትኩ። “ምን
ያህል እንደምወድሽ ብታዉቂ!” አልኩ በልቤ! ግን ህይወት
የእዉነታ እንጂ የስሌት ጉዳይ አይደለችምና እዉነቱን
ማስተናገዱ ይሻላል።
ስለዚህ ነገር አልተነገረኝም ነበር። የሪቾን ግጥሞች በዚህ
መልኩ ሳያቸዉ እንድደመም አስባ ይሆናል ሀዩ
ያልነገረችኝ። የራሄል ቤተሰቦች ባዩት ነገር በጣም
ተደምመዋል። ምን እነሱ ብቻ እኔ ራሱ የሌለ
ተደንቄያለሁ። ሌላዉ በጣም የሚገርመዉ ራሄል ለእኔ
የፃፈችዉ የስንብት ደብዳቤ በትልቁ ግድግዳዉ ላይ
የተፃፈበት ልዩ የመመገቢያ ክፍል መኖሩ ነዉ። ስገምት
ሴቶች ባላቸዉን ለመጋበዝ የሚመርጡት ሁነኛ ቦታ
የሚሆን ይመስለኛል። ስታጣኝ እዉነቱን ትጋፈጣለህ
አይነት ማስፈራሪያ ሲፈልጉ ማለት ነዉ።
በሀዩ የአመራር ብቃት ተደመምኩ። በቀጣይ ደግሞ ሆቴሉ
የአስጎብኚ ቡድን እንዲኖረዉ ለማድረግ አቅደዋል። ሀዩ
ታቅዳለች እኔ እየሳቅኩ እፈርማለሁ።
.
ጉብኝቱን ጨርሰን ምግብ ልንበላ የምግብ አዳራሹ ዉስጥ
ስንገባ ሰዒዶናኢማን ይዘዉኝ ያደረግከዉ ንግግር
የፖለቲከኛ ይመስላል ብለዉ ፎገሩኝ። ሰኢዶናኢማን አንድ
ወንድ ልጅ ወልደዋል። ሙሀባ ብለዉታል። የራሄል አባት
በተሰራዉ ስራ የተሰማቸዉን ደስታ ገለፁልኝ። ወዲያዉ
አንድ የራሄል ቤተሰብ የሆነ ልጅ መጥቶ አድናቆቱን
ከገለፀልኝና በዚህ እድሜዬ እንደዚህ ለስኬት መብቃቴ
እንደገረመዉ ነግሮኝ ጥያቄ አዘነበብኝ። እሱ ሀብቴ
ብዙዉን የዉርስ መሆኑን አያዉቅም። ሲቀጥል ሆቴሉን
በዚህ መልኩ የማስተዳድረዉ እኔ መስየዋለሁ። ሀዩ
እንደሆነች አያዉቅም።
“አንድ ቆንጆ ምክር እስኪ ምከረኝ!” አለኝ ከኔናከሀዩ ጋር
እየተቀመጠ
“በወንድናበሴት መካከል ተፈጥሯዊ መፈላለግ አለ።
ስለዚህ ሴት ልጅ ሚስትህ እንጂ የልብ ጓደኛህ አትሁን!”
አልኩት። ሀያት ሳቋን ለቀቀችዉ። እኔ ጓደኞቼ ሴቶች
በመሆናቸዉ የገባሁበትን ጭንቅ እኔ ነኝ የማዉቀዉ።
ራሄል ጓደኝነት በቀደደዉ መንገድ ፍቅር ላይ ወድቃ ነዉ
እስከሞት የደረሰችዉ።
“አንተ ጓደኛህን አይደል እንዴ ያገባኸዉ?” አለኝ ወደ ሀያት
እየጠቆመ
“አዎ ግን የሞተችዉም ጓደኛዬ ናት።” አልኩትና ወደ ሀዩ
እየጠቆምኩ “እሷም ብትሆን ደስታዬ የሆነችዉ ከተጋባን
በኋላ ነዉ።” አልኩት።
ልጁ ፈገግ ብሎ ልጃችንን እና ከኛ ቀጥሎ ያለዉ ጠረጴዛ
ላይ የተቀመጡትን ቤተሰቦቻችንን እያየ ሳቀና “የናንተ
ቤተሰብ በጣም ያስቀናል!” ብሎን እየሳቀ ከመቀመጫዉ
ተነስቶ ወደ ቤተሰቦቻችን ጠረጴዛ ሄደ። የልጁ ድፍረት
ገረመኝ። ራሄል በወንዱ ነገር ነዉ። ከእናቴ ጋር ማዉራት
ጀመረ። ስቀን ዞር አልን።
.
ከሁለት ቀን በኋላ እኔ መኝታ ክፍል ዉስጥ ጋደም
ብያለሁ። ሀዩ ራህማን ስታጫዉት ይሰማኛል። የምትለዉን
ራህማ እንድትደግመዉ እያደረገች ትስቃለች።
“ረበና” አለች ሀዩ
“አፐና” ትላለች ራህማ! ሀዩ በሳቅ ፍርስ ትላለች
“ማ ኸለቅተ ሀዛ”
“ማተዛ” ትላለች ራህማ! አሁን እኔም በጣም መሳቅ
ጀምሬያለሁ። ሀዩ በጣም እያዝናናት ነዉ መሰለኝ
ቀጠለች።
“ባጢለን ሱብሀነክ!”
“ባክነን” አለች ራህሚ! በሷ ቤት ሀዩ ያለችዉን መድገሟ
ነዉ። አንደበቷ ይጣፍጣል። ከምር ግን እንደ ልጅ ምንም
የሚያስደስት ነገር የለም። ሀያት ራህማን ስታስብላት
የነበረዉ የቁርዓን አንቀፅ ነዉ። “ረበና ማ ኸለቅተ ሀዛ
ባጢለን ሱብሀነክ!” ነበር ያለችዉ። ትርጉሙ “ጌታችን
ሆይ ይህን (ድንቅ አለም) እንዲሁ (ያለ ዓላማ)
አልፈጠርከዉም …” ማለት ነዉ። ፈጣሪ ምድርና ሰማይን
እንዲህ ያስዋበዉ የስዕል ጥበቡን ለማሳየት አይሆንም።
ስለዚህ በከንቱ ያልተፈጠረ ምድር ላይ ከንቱ መሆን
አይገባም። ምድር በከንቱ አልተፈጠረችም። እኛም
ለጨዋታ አልተፈጠርንም። ህይወታችን ቁምነገር ሊሆን
ይገባል!! “የራሄል አምላክ እዉነት ተናገረ!” አልኩ አልጋዉ
ላይ እንደተዘረርኩ። አልረሳት ነገር ከልቤ ታትማ ፤ የኔ
አትሆን ነገር ከመቃብር ከትማ! ጌታዬን ራህማን እና
ሀያትን ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ። የተከለከልናቸዉ
ከሚመስሉን ነገሮች ይልቅ የተሰጡን ዋጋ አላቸዉ።
.
ተፈፀመ

መንታ መንገድ ክፍል 14

መንታ መንገድ
ክፍል አስራአራት

.
.
ራሴን ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ አላዉቅም ነበር።
አይኔን ስገልጥ ነጭ አምፖል ሰማያዊ ኮርኒስ ላይ
ይታየኛል። ወዲያዉ ቀና ስል ከፊት ለፊቴ ሰዒድ እና
ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉዬ እየተመለከቱኝ ነበር።
ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉ ወዲያዉ ጌታዬን
እንዳመሰግን አዘዘኝ። አመሰገንኩ። ወዲያዉ ወደ ጆሮዬ
ተጠግቶ ለስግደት ጥሪ የሚደረገዉን አዛን እያደረገ
የማጅራቴን ደምስሮች በጣቱ ነካካቸዉ።
“ሴቶች በጣም ይወዱህ ነበር?” አለኝ ኡስታዙ ሰዒድ
አጠገብ እየተቀመጠ
“እንደዛ ነገር” አልኩት።
“ያይኔአበባ የምትባል ሴት ታዉቃለህ?” አለኝ አይን አይኔን
እያየ።
“አዎ ዩኒቨርሲቲ ስማር የምጠቀምበት ምግብ ቤት
አስተናጋጅ ናት።” አልኩት።
ሰዒድ በግርምት አንገቱን ነቀነቀ። ኡስታዙ “እዛ ቤት
በጣም ጣፍጦህ የበላህበት ቀን ትዝ ይልሀል?” አለኝ።
እንደድንገት አንድ ቀን የበዓል ስጦታ ብላ ያይኔአበባ
የሰጠችኝ ምግብ ትዝ አለኝ። እንደዉም ብቻዬን ዶርም
ነበር የበላሁት። ኡስታዙ ሌሎች ጥያቄዎችንም ጠይቆኝ
ከመለስኩለት በኋላ ድግምቱ የተሰራብኝ በያይኔአበባ
እንደሆነ ነገረኝ። ያይኔአበባ ወዳኝ እንደነበር ግን
ልትፎካከራቸዉ በማትችላቸዉ ቆንጆ ሴቶች ተከብቤ
የነበረ በመሆኑ ድግምት እንዳሰራችብኝ ራሴን በሳትኩበት
ሰዓት ዉስጤ የነበረዉ ጋኔን መናገሩን አረዱኝ። ኡስታዙ
አሁን በፈጣሪ ፈቃድ ድግምቱ መክሸፉንና ዉስጤ
የነበረዉ መጥፎ ስሜትም እንደሚወገድ አበሰረኝ።
በሀይማኖቴ መጠንከር እንደሚኖርብኝ መክሮ ከግብረስጋ
ግንኙነት በፊት ላደርጋቸዉ የሚገቡ ነገሮችን መከረኝ። .
በተፈጠረዉ ነገር እኔም ሰዒድም ተገርመናል። መኪና
ዉስጥ እንደገባን ሰዒድ “በል እስኪ ዛሬ ሂድና ሞክራት
እና ጉዱን እንየዉ!” አለኝ እየሳቀ። እዉነት ለመናገር
በጣም ቅልል ብሎኛል።
.
ማታ ቤት ስገባ ሀዩ አኩርፋ መጅሊሱ ላይ ተቀምጣለች።
ደሞ ምን ተፈጠረ? “ሀዩዬ ምን ተፈጠረ?” አልኳት ከጎኗ
እየተንበረከክኩ።
“አክረሜ ልዉለድልህ ፍቀድልኝ!” አለች እያለቀሰች።
የአልጋ ላይ ፀባዬ እስኪስተካከል ላለመዉለድ ወስኜ
መድሀኒት እንድትወስድ አዝዣት ነበር። አይ ሀዩ! ከነዚህ
የአልጋ ላይ ፀባዬ ምንም ሳትጠላኝ ልትወልድልኝ መጓጓቷ
የፈጣሪ ስጦታ እንደሆነች እንዳስብ አደረገኝ። ፈገግ
አልኩና “አላህ ካለ ነገ ጠዋት መልሴን እነግርሻለሁ!”
አልኳት ዛሬ ማታ ሊፈጠር የሚችለዉን ሰላማዊ ለሊት
ተስፋ እያደረግኩኝ።
.
ማታዉን ኡስታዙ በነገረኝ መልኩ ግንኙነት ከመፈፀማችን
በፊት ሰግጄ ፀሎት አደረስኩ። ከዛም የሀዩ ጭንቅላት ላይ
መዳፌን አስቀምጬ ጌታዬን ለመንኩ። ዉስጤ በእርጋታ
ተሞልቷል።
ሀዩን ሳምኳት ፣ እጄ ጥፊ እንዳይቀድመዉ ፈርቼያለሁ።
እየተሳሳምን በስሜት ጠፋን። እጆቼ ሰዉነቷ ላይ
ተንሸራሸሩ። ልክ እንደሰዉ ተገናኘኋት። ሀዩ ፊቷ በእርካታ
ተሞልቶ እየሳቀች “ጌታዬ እንደማያሳፍረኝ አዉቅ ነበር።”
አለችኝ። የረዥም ጊዜ ፀሎቷ ይሄ ነበር መሰለኝ።
ሁለታችንም መድገም ፈለግን! ሀይል አሰባስበን
ደገምነዉ። እርካታ ጣራ ነካ! ማመን ከበደኝ። የምድርን
ጣፋጩን ነገር በእርጋታ ማጣጣም ቻልኩኝ። ሀዩ እቅፌ
ዉስጥ ቀለጠች። ፍልቅልቅ እያለች “አፈቅርሀለሁ።”
አለችኝ። ጌታዬን አመስግኜ ሀዩን እቅፍ አድርጌ ተኛሁ።
.
በነጋታዉ ጠዋት ሀዩ ከእንቅልፍ እንደተነሳን የወሰደችዉ
የመጀመሪያዉ እርምጃ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖችን
መጣል ነበር። አሁን ልጅ ያስፈልገናል። ጠዋቱን ሰዒዶ
ደወለና “እ ጄኪጃን አደብ ገዝተህ አደርክ ወይስ?” አለኝ።
“ኧረ አልሀምዱሊላህ ዛሬ ጥፍጥናን አጣጣምኩት። አሁን
ከልቤ እንድትቀምሰዉ ተመኝቼልሀለሁ።” አልኩ