መንታ መንገድ ክፍል 9

ክፍል ዘጠኝ
.
.
ሀያት ከራሄል ጋር ከባጃጅ ስወርድ ካየችበት ቅፅበት በኋላ ስልክ ስደዉልላት አታነሳም። በነጋታዉም ወደ ክፍል አልመጣችም። በጣም ጭንቅ አለኝ። ራሄል ልታገኘኝ ስልክ ብትደዉልም ማንሳት አልፈለግኩም። ክፍል ዉስጥ ስንገናኝ እናወራለን። ራሄል ምንም አላጠፋችም ግን ሀያትን እንደነጠቀችኝ ተሰማኝ። አሁን ከራሄል እና ከሀያት ትክክለኛዋ ምርጫዬ ሀዩ መሆኗን የተፈጠረዉ ክስተት በደንብ አረጋግጦልኛል። ዶርም ብቻዬን ተቀምጬ ከሀዩ ጋር ያሳለፍናቸዉን አስደሳች ጊዜዎች አስባለሁ። በተለያዩ የሀገራችን ክልሎች ባደረግናቸዉ ጉዞዎች ዉስጥ ያሳለፍናቸዉ ወርቃማ ጊዜያት አይኔ ላይ ድቅን ይላሉ። የሀያት ፍልቅልቅ ሳቅ አይኔን ይሞላዋል። በጨዋነቷ የታጀበዉ ፈገግታዋ ትዉስ ይለኛል። ምራቋን እየዋጠች “የሌላ ስትሆን ካየሁ ግን ሰዉ አልሆንም!” ያለችኝ ትዝ ይለኝና በራሴ እበሽቃለሁ። አዎን ሀዩ እንደድሮዉ ደስተኛናተጫዋች መሆን ከብዷታል። በርግጥ ከራሄል እና ከሀያት አንዷን ሳልመርጥ በዝምታ የቆየሁት ጓደኝነታችን ሊበጠበጥ ይችላል በሚል ስጋት ነበር። ዉጤቱ ግን ፉክክር ሆኖ አረፈዉ። ፉክክሩ ደሞ ጨዋዋ ራሄልን ራሱ ራቁቷን ፊቴ እስከመቆም አደረሳት። እዉነታዉን ልመልከት ብል ኖሮማ ሀያት ከራሄል ጋር የማትነፃፀርበት አንድ ትልቅ ከኔ ጋር የሚያመሳስላት ነገር አላት። ሀይማኖታችን አንድ አይነት ነዉ። እኔ ደሞ ሀይማኖቷ ከኔ የተለየችን ሴት አላገባም። አንቺም በሀይማኖትሽ እኔም በሀይማኖቴ የሚለዉ አባባል የሚያምረዉ ዘፈን ላይ ብቻ ነዉ። መቻቻልን ለማሳየት የሀገር መሰረት የሆነዉ ቤተሰብ መናጋት የለበትም። ትዳር ልጅ የሚባል ፍሬ የሚያፈራ ተቋም ነዉ። ልጆችን ወደ አንዱ ሀይማኖት ለመዉሰድ በሚደረገዉ ሽኩቻ መሀል ልጆች ችግር ዉስጥ ሊገቡ አይገባም። ትዳሩም በሆይሆይታ ይጀመር ይሆናል እንጂ ባለመስማማት መጠናቀቁ አይቀርም። እስልምና ደግሞ የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ማግባትን አይፈቅድም።
.
ሀዩን የተፈጠረዉ ነገር ላይ እጄ እንደሌለበት ለማስረዳት ቢያንስ እንዳገኛት ልትፈቅድልኝ ይገባ ነበር። እሷ ግን ስልኳን እንኳ አታነሳም። እንደ ድሮዉ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት አብሮ መብላት ቀረ። መንገድ ላይ ካየችኝ ራሱ መንገድ ትቀይራለች። ሀጅራ ሀያትን አንዴ እንኳን የምናገረዉን እንድትሰማኝ እንድታስማማት ብጠይቃትም ሊሳካላት አልቻለም።
.
ጁምዓ(አርብ) ትልቁ ኦዲተሪየም ዉስጥ የሚካሄደዉ የስነ ፅሁፍ ምሽት ላይ ስራዎቻችንን ለማቅረብ ከራሄል ጋር ሄድን። ዝግጅቱ ተጀምሮ ታዳሚዉ ቦታ ቦታዉን ከያዘ በኋላ ሀያት እና ሀጅራ ገብተዉ ከአቅራቢዎች መቀመጫ በስተግራ በኩል ራቅ ብለዉ ተቀመጡ። ከራሄል ጋር አብረን ያደርን ጊዜ የፃፍኩትን ግጥም ባቀርብ ለሀያት እዉነቱን ለማስረዳት እንደሚረዳኝ አሰብኩ። ገጣሚዎች እየተጠሩ ስራቸዉን ማቅረብ ጀመሩ። የሪቾ ተራ ደረሰና ወደ መድረኩ ወጣች።
“ስርየት” ብላ የግጥሙን ርዕስ አስተዋወቀችና ጉሮሮዋን ከጠረገች በኋላ ግጥሙን ማንበብ ጀመረች
“የታመመ ልቤን የሚያሽረዉ አጥቶ፣
ዘወትር ሲሰቃይ መድሀኒትን ሽቶ፣
በአንድ ለሊት ፍቅር፣ ቁስሉን አጠፋኸዉ፣
በእጅህ ልስላሴ ፣ገላዬን አከምከዉ፣
በከንፈርህ ጠዓም፣ ምሬትን ገደልከዉ፣
ገላዬ ላይ ነግሰህ ፣ ሰላሜን መለስከዉ።
ልቤ ሰላም ሲያገኝ ፣ ሀሴት ሊያገኝ ነብሴ፣
ጉድለቴን ሚደፍን ፣ የሰመመን ልብሴ
ተቸረኝ ከፍቅርህ ፣ ጠፋን ምድርን ለቀን፣
ስርየት ሆነ ያኔ ፣ ፍቅርህን ስትቸረኝ!
የኔ ነሽ ስትለኝ! ” አለችና ወደ ቀጣዩ ግጥም ለመሻገር ወረቀቱን ገለፀችዉ። ሀያት ከዚህ በላይ ለመቆየት አቅም አጣች። እንባዋን በሂጃቧ እየጠረገች አዳራሹን ለቃ ወጣች። ሀጅራም ተከተለቻት። ይሄ ግጥም ሆነ ተብሎ ለሀያት አክረምን አንሶላ ተጋፍፌዋለሁ ብላ ለማሳመን ያቀረበችዉ መሆኑ ገብቶኛል። ደግሞም ተሳክቶላታል። እኔም ግጥም የማቅረብ እቅዴን ሰርዤ አዳራሹን ለቅቄ ወጣሁ። ዉጪ ላይ ሀጅራ ሀያትን አቅፋ ስታባብላት አገኘኋቸዉ። ልጠጋቸዉ ስል ሀጅራ ራሷ እንድርቅ በእጇ ምልክት ሰጠችኝ። ከሀያት ጋር ለመነጋገር ጥሩ ሰዓት አይደለም ብላ ስላሰበች ይመስለኛል እንድርቅ ምልክት ያሳየችኝ። ቆይ እኔንስ ማን ይረዳኝ? ለምን አንዴ እንኳን እንዳወራት አትፈቅድልኝም? ለምን? ብስጭቴ ጣራ ነካ። ወደ ዶርም ሄጄ ማንም እንዳያናግረኝ ተናግሬ በብርድልብሴ ተጠቅልዬ ተኛሁ። እንቅልፍ ግን የለም!
.
ጠዋት ላይ ሀጅራ ደወለችልኝ። የዛሬን አያድርገዉና ሌላ ጊዜ በዚህ ሰዓት ሀዩ ደዉላ ቁርስ አረፈድክ እያለች ትበሳጭብኝ ነበር። ሀያት እና ራሄል ላይ ላዩን ሰላም ናቸዉ ግን ዉስጥ ዉስጡን እንደድሮዉ አይመስሉኝም። ስልኩን አንስቼዉ “ሀጁ በአላህ ሀያት ላናግረዉ አለች በይኝ!” አልኳት። ምኞቴ ነበር።
“ወይ ላናግረዉ¡ ባክህ ወደ ቤት ልትመለስ ሻንጣዋን እያዘገጃጀች ነዉ የሆነ ነገር አድርግ።” አለችኝ። ሀዩ ፀፀቴን ከአቅሜ በላይ ልትከምርብኝ ነዉ! የክፍላችንን ሰቃይ በኔ ምክንያት ወደ ቤቷ ስትመለስ ከማይ ብሞት እመርጣለሁ።
“አሁን ዶርም ናት?” አልኳት ሀጅራን
“የደወልኩልህ ቁርስ ልንበላ ከግቢ ልንወጣ ስለሆነ ነዉ። እንግዲህ የሆነ ነገር አድርግ። ያለበለዚያ ትኬት ቆርጣ ወይ ዛሬ አሊያም ነገ እሄዳለሁ ብላለች።” አለችኝ። ሀዩ የሌላ ስሆን ካየችኝ ሰዉ እንደማትሆን አስቀድማ ነግራኝ ነበር። ትምህርት እስከማቋረጥ የሚያደርስ ህመም እንደፈጠርኩባት ሳስብ በጣም በራሴ ተበሳጨሁ። ሀዩን ማስቀረት ካልቻልኩ እኔ ራሴ ሰዉ አልሆንም። ሀጅራ ሲወጡ ሚስኮል እንድታደርግልኝ ተነጋግረን ስልኩን ዘጋችዉ።
.
ይገርማል ሀዩን ከአጠገቤ ማጣት እንዲህ ያመኛል ብዬ አስቤ አላዉቅም። በአቅራቢያችን ያሉ መልካም ነገሮችን ጥቅም የምንረዳዉ ስናጣቸዉ ነዉ።
ራሄል ደዉላ አብረን ቁርስ እንድንበላ ጠየቀችኝ። ራሄል በፉክክሩ ምክንያት በጓደኝነታችን መሀል የተፈጠረዉ ክፍተት እሷንም በጣም አሳስቧታል። እኔ ግን የሀጅራን ስልክ እየጠበቅኩ ስለነበር መብላት እንደማልፈልግ ነገርኳት። ራሄል ብዙ ጊዜ አልበላም ካልኳት ዉጪ ወጥታ በስርዓቱ አትበላም።
ሀጅራ ሚስኮል ስታደርግልኝ ከዶርም ተነስቼ ከግቢ ዉጪ ወዳሉት ምግብ ቤቶች ሄድኩ። ሀያት እና ሀጅራ ሁሌም የምንበላበት ቤት ቁርስ አዘዉ ተቀምጠዋል። ያይኔአበባ ለማስተናገድ ትንደፋደፋለች። የምትሰራዉ ምግብ ይጣፍጣል። ከኔ ጋር ደሞ ስለምንግባባ አንዳንዴ ቆንጆ ምግብ ስትሰራ እንድቀምስላት በእቃ ትሰጠኛለች። ሀያት እና እኔ ሁሌም ሳንዱች በወተት ነበር ቁርስ የምንበላዉ። ከነሀያት ፊት ለፊት ተቀመጥኩና ያይኔአበባን እያየሁ “ሳንዱችናወተት” አልኩ! ሀያት ቀና ብላ ስታየኝ ፊቷ ተቀየረ። ጠልታኛለች። ግን እዉነቱን ለማስረዳት ከዚህ የተሻለ ጊዜ አላገኝምና ከነበርኩበት ጠረጴዛ ተነስቼ ሀያት አጠገብ ተቀመጥኩ።
ሀዩ ምራቋን ዋጥ አደረገችና “ምን ፈለግክ?” አለችኝ።
“ሀዩ በአላህ ይሁንብሽ አንዴ ብቻ አዳምጪኝ! አንዴ ብቻ! ላስረዳሽ!” አልኩ በአይኔ እየተለማመጥኳት።
ሀዩ የንዴት ፈገግታ ፈገግ አለችና እንባዋ እየቀደማት “እንዴት እንደሳምካት ነዉ የምታስረዳኝ? እንዴት እንደረከስክላት ነዉ ወይ የምታብራራልኝ? ከኔ ጋር ለትዳር ለመተጫጨት ዝሙት ላይ እንዳንወድቅ እናትሽ ይኑሩ ምናምን አልክ። ከኔ ጋር ስትሆን ሀይማኖተኛ ሀይማኖተኛ ይሰራራሀል። እኔ እኮ በክብር አግባኝ ነበር ያልኩህ! የማግባት አቅሙ ነበረህ። ግን አንተ የትም መልከስከስን ነዉ የመረጥከዉ። እና ምኑን ነዉ የምታስረዳኝ?” አለችና እንባዋን በሂጃቧ ጠ

ርጋ ቀጠለች
“አክ

ረም ከአንተ ጋር ብዙ ህልም ነበረኝ። ቀጣይ ህይወቴን ያለምኩት አንተን የህይወቴ አንድ አካል አድርጌ ነበር። ሁሌም ከእንቅልፌ ስነሳ ማየት የምፈልገዉ አንተን ነበር። ዛሬ ግን ለአይኔም አስጠልተኸኛል። ደግሞም በፍፁም የኔ መሆን አትችልም!” አለችኝ። የኔ መሆን አትችልም ያለችኝ የማልወዳት መስሏት ከሆነ ብዬ “ለምንድነዉ ያንቺ የማልሆነዉ?” አልኳት።
ሙሉ አካሏን ወደኔ እያዞረች “ዝሙተኛ ወንዶች የዝሙተኛ ሴቶች ናቸዉ። የምትለዉን የቁርዓን አንቀፅ እኮ አንተዉ ነበርክ የምትደጋግማት። አሁን ቆሽሸሀል ለንፅህናዬ አትገባም። የኔ ላድርግህ ብል ፀቤ ከፈጣሪ ጋር ነዉ የሚሆነዉ።” አለችኝ። ሀዩ ስታወራ የከዳኋት ባሏ እንጂ ገና ለፍቅር የጠየቀችኝ አትመስልም። አንባገነን ናት። ሪቾ ግን ለማሸነፍ ነዉ የምትሞክረዉ እንደ ሀዩ አታለቃቅስም።
ዝም ብዬ ሳዳምጣት የነበረዉ ሴቶች እንደዚህ በስሜት ሲያወሩ ከወንዱ የሚፈልጉት ትኩረቱን እንጂ መልሱን አይደለም ብዬ ስላሰብኩ ነዉ። ስትጨርስ ቀስ ብዬ ማስረዳት ጀመርኩ። “አዎን ቆሻሻ ወንዶች የቆሻሻ ሴቶች ናቸዉ። ግን እኔም ራሄልም ቆሻሻዎች አይደለንም።” አልኳት።
“እንዴት ባክህ?” አለችኝ እያፈጠጠችብኝ። አሁን ለማዳመጥ ዝግጁ መሆኗ ስለገባኝ እኔናራሄል ዝሙት አለመፈፀማችንን እና የዛን ቀን የተፈጠረዉን ነገር አንድም ሳላስቀር አስረዳኋት።
ሀያት እንባ በእንባ ሆነች። ከተቀመጠችበት ብድግ አለችና መሬቱ ላይ በግንባሯ ተደፍታ ጌታዋን አመሰገነች። ለኔ ንፅህና ጌታዋን የምታመሰግን ሴት! እንደሀያት ያሉ ሴቶች ከሚሊየን አንድ ናቸዉ።
.
ቁርሱ እንደቀረበ ሀዩ እንደለመደችዉ የኔን ቆርሳ በላችብኝ። ደስ አለኝ። ታርቃኛለች ማለት ነዉ። ወዲያዉ “አኩሻ ግን” አለች።
“ግን ምን?” አልኳት ፈገግ እያልኩ።
“አሁን ታረቅን ብቻ ነዉ ሚባለዉ ወይስ?” አለች አይኗን በሀፍረት እየሰበረች።
ምን ለማለት እንደፈለገች ስለገባኝ “ሴሚስተሩ ሲያልቅ ኒካህ እናደርጋለን። እኔም ከአሁኑ ቤት እናገራለሁ አንቺም ንገሪያቸዉ።” አልኳት። በደስታ ልታብድ ምንም አልቀራትም። ወዲያዉ ስልኳን አንስታ ራሄል ጋር ደወለችና ጠራቻት። ሪቾ ስትመጣ እኔም እዛዉ አለሁ። አየችንና “ኦ ገባኝ ሀዩ አሸነፈች ማለት ነዉ?” አለችኝ። “አዎ” አልኳት አይን አይኗን እያየሁ። ሪቾ በጣም ፍትሀዊ ናት! አታለቃቅስም። ግን በጣም ትወደኛለች። እኔም ሀይማኖታችን ቢመሳሰል የመጀመሪያም የመጨረሻም ምርጫዬ ሪቾ ነበረች።
ራሄል እንደምንም ፈገግ አለችና “እንደዚህ አራታችንም የምንሰበሰብበት ቀን ናፍቆኝ ነበር።” አለች። ከዛም ራሷ የዛን ቀን እንዴት ዉጪ አብሬያት እንዳድር እንዳደረገችኝ ፣ ሀዩን ለማሳመን የተጠቀመቻቸዉን መንገዶች ተረከችልን። ሪቾ ሽንፈቷን በፀጋ መቀበሏ በጣም አስደሰተኝ። ሪቾ እኮ ጨዋ ናት ብያችሁ ነበር። ከቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አራታችንም እንደድሮዉ አንድ ላይ ቁርስ በላን።
.
ይቀጥላል…

መንታ መንገድ

መንታ መንገድ
ክፍል ስምንት

.
.
ባህርዳር ፓፒረስ ሆቴል ከራሄል ጋር አንድ ክፍል ዉስጥ ነን። ራሄል ሙሉ ራቁቷን ከፊት ለፊቴ አልጋዉ ጋር ቆማለች። በሩን ተደግፌ አየኋት። አንድ ከዉብም ዉብ የሆነች ለፍቅር የምትከጅለኝ ሴት መቋቋም የማልችለዉን ዉበቷን ከፊቴ ደቅናብኛለች። የሴት ልጅ ራቁት ገላን የሚደርስ ዉበት ምድር ላይ ለመኖሩ እጠራጠራለሁ። እኔ እንኳን ዝሙት ልፈፅም ከቤተሰቤ ዉጪ የሆነች ሴት ልጅን እንኳ ጨብጬ አላዉቅም። ጨዋነቴን ደሞ ራሄል ራሷ ትመሰክራለች። ራሄል በእጆቿ እንድቀርባት ምልክት እያሳየች ተጠጋችኝ። ምን እያደረገች ነዉ? ልቤ ቀጥ አለ። ተጠጋችኝ! አተነፋፈሴ ዝብርቅርቁ ወጣ። በጣም ቀረበችኝ! ተሸነፍኩ። ያለምንም ጦር መሳሪያ በራቁት ገላዋ አስገዳጅነት ልብሴን ራሴዉ ማዉለቅ ጀመርኩ። “አክረም ሀይማኖትህስ?” ይላል ህሊናዬ! “ሀይማኖት ምን ነበር? ሀይማኖት? ሀይማኖት? አላወቅኩትም!” ብዬ እክዳለሁ። ህሊናዬ ጥያቄዉን አያቆምም “እሺ ሀይማኖተኛ አይደለህ ጌታህን አትፈራዉም?” ይለኛል። “ጌታ ማነዉ?” ብዬ የትም እንደማላዉቀዉ ለህሊናዬ እነግራለሁ። የሴት ዉብ ገላ ከፊትህ ቀርቦ ፈጣሪህን ልታስብ አትችልም። አሁን የፈጣሪ ትዕዛዝ በደንብ ገባኝ። ለምን ዝሙትን አትቅረቡ እንጂ አታድርጉ የሚለዉን ቃል እንዳልተጠቀመ ተረዳሁ። ዝሙት ደጃፍ ላይ ተቁሞ ዝሙትን አልሰራም ማለት ዘበት ነዉ። ራስን ነፃ ለማዉጣት ዉሳኔ የመወሰን አቅም የሚኖረን በሩ ላይ ሳንደርስ ከሩቁ ሲሆን ብቻ ነዉ። ነብዩ ዩሱፍ(ዮሴፍ) እራሱ የዝሙት ግብዣ እሱናጋባዧ ብቻ በነበሩበት ዝግ ቤት ዉስጥ የቀረበለት ጊዜ ልቡ ከጅሎ ነበር። ግን ነብይ ነበርና ፈጣሪ የነገሩን መጥፎነት አመላከተዉ።
ራሄል ቦዲዬን በማዉለቅ ተባበረችኝ። ሁለታችንም ራቁታችንን ቆምን። ራሄል እጄን እየጎተተች ወደ አልጋዉ ወሰደችኝ። አንገቴን ይዛ ወደ ከንሮቼ ከንፈሮቿን አስጠጋች። አንዴ ስትስመኝ ሰዉነቴን ለየት ያለ የቁጣ ስሜት ወረረዉ። በጥፊ ብዬ አልጋዉ ላይ ዘረርኳት። ሪቾ በጣም ደነገጠች። እኔ ግን አሁንም ፍላጎቴ እንዳለ ነዉ። ወደ አልጋዉ ስወጣ ሪቾ ተፈናጥራ ከአልጋዉ ወረደችና ልብሷን እንደነገሩ ለባበሰች። ምንድነዉ የተፈጠረዉ? ለምን በጥፊ መታኋት? ልቤ እኮ ሊያቅፋት ነበር የፈለገዉ። አካሌን ማን አዘዘዉ? ግራ ገባኝ። ሪቾ በግርምት ቆማ አየችኝና “በጣም ይቅርታ!” አለችኝ። ምን ብዬ የተፈጠረዉን ነገር እንደማስረዳት አላዉቅም። “ልመታሽ ፈልጌ አልነበረም!” አልኳት ቱታ ሱሪዬን እየለበስኩ። አንዳችን ጭንቅላታችንን በላይ በኩል ሌላችን በታች አድርገን በተለያየ አንሶላ ለመተኛት ተስማማን። ሪቾ በጥፊ የመታኋት ከሷ ጋር መተኛት ስላልፈለግኩ እንደሆነ አስባ ያቀረበችዉ አማራጭ ነዉ። እኔ እጄን ማን እንዳዘዘዉ አላዉቅም እንጂ እንቢ የምልበት ምንም አቅም አልነበረኝም።
.
ልክ በተቃራኒ አቅጣጫ እንደተኛን ሪቾ “አክረሜ ይሄ አንተን የኔ ለማድረግ የወሰድኩት እርምጃ ነበር። ባለጌ አይደለሁም ታዉቃለህ! ግን ፉክክሩ ከሀያት ጋር ሆነና በጣም ከበደ። ስለዚህ አንተን ለማሳመን ጊዜ ከመፍጀት ይልቅ እሷን በፈቃዷ እንድትተዉህ ማድረግ ነበረብኝ። ሀያት ዛሬ የተፈጠረዉን ነገር ስታዉቅ ራሷ ትተዉሀለች። ያኔ የኔ ብቻ ትሆናለህ።” አለችኝ።
ንግግሯ ዉስጥ የተጠና ስሌት ነበር። “እና ዉጪ አምሽተሽ አብረን እንድናድር ያደረግሽዉ አዉቀሽ ነዉ?” አልኳት ብሽቅ እያልኩ።
ተንጠራርታ ቦርሳዋን ከአልጋዉ ጎን ካለዉ ጠረዼዛ ላይ አነሳችና ከዉስጡ ብዙ መቶ መቶ ብሮችና ኤቲኤም ካርድ አዉጥታ እያሳየችኝ “አይደለም አንድ አንድ ክፍል ሁለት ሁለት ክፍል የሚያስይዝ ብር ይዤ ነበር። ግን እድሉን መጠቀም ነበረብኝ።” አለች። ወንድ ልጅ ከሴት ልጅ ጋር በተንኮል ሊፎካከር አይችልም። ሴትም ወንድን በጉልበት ልታሸንፍ አይቻላትም። አሁን ሪቾ ሁሌም ትለኝ የነበረዉ ነገር ትዝ አለኝ። “እኔ አንተን የራሴ ለማድረግ ምን ያህል መስዋዕትነት የምከፍል ይመስልሀል?” ነበር የምትለኝ። ዛሬ የት ድረስ እንደምትሄድ በተግባር አሳየችኝ። አሁን ሀያት ይህን ጉድ ካወቀች ምንም አልፈፀምንም ብላት እንዴት ነዉ የምታምነኝ? አንድ አልጋ ላይ ተኝተን ሳልነካት ወጣሁ ብላት እንዴት ነዉ የሚዋጥላት? እሷ ብትሆን ያደረገችዉ እኔም አይዋጥልኝም ነበር።
.
ሰማይ ሊጠራ ሰዓቱ 11:00 ሲል ከእንቅልፌ ባነንኩ። ሁሌም በዚህ ሰዓት የንጋት ስግደት ስለምሰግድ ከእንቅልፌ እነሳለሁ። ሪቾ ቀልቧን ስታ ተኝታለች። ፀጉሯ ብትንትን ብሎ ፊቷን በከፊል ሸፍኖታል። ግንባሯን ልስማት ፈለግኩና ትነቃለች ብዬ ፈርቼ ተዉኩት። አንዱን እግሯን እግሬ ላይ ሰቅላዋለች። ከንፈሮቿ ያሳሳሉ። ከዚህ በላይ ካየኋት እንዳልሳሳት ስለፈራሁ አይኔን ሰብሬ ሪቾን ላለመረበሽ እየተጠነቀቅኩ ከአልጋዉ ወርጄ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄድኩ። መጀመሪያ ገላዬን ከታጠብኩ በኋላ ዉዱዕ አድርጌ ከመታጠቢያዉ ወጣሁ። “ዉዱዕ” ከስግደት በፊት የሚደረግ ትጥበት ነዉ። ጃኬቴን መሬት ላይ አንጥፌ ሰገድኩ። ከወንጀሎች ሁሉ ከባዱ ወንጀል ዝሙት አፋፍ ላይ የተሰገደን ስግደት ፈጣሪዬ ይቀበለኝ ይሆን? አላዉቅም። ሪቾ አሁንም እንደተኛች ናት። ቀን የበላችዉ ምግብ አልተስማማትም መሰል ደጋግማ ትፈሳለች። ገረመኝ! የእዉነት ቆንጆ ሴቶች የሚፈሱም ሆነ የሚፀዳዱ አይመስለኝም ነበር። መልዓክ ነዉ የሚመስሉኝ። ሽንት ቤት ደርሰን እንምጣ ሲሉ ራሱ መስታወት ላይ ፀጉራቸዉን ለማስተካከል እንደሆነ ነበር የማስበዉ። እንደዉም ሲመስለኝ ይሄ የኔ ብቻ ሳይሆን የብዙ ባለትዳሮች ችግር ነዉ። ቆንጆ ናት ብሎ ያገባና እንደሰዉ ስትሳሳት አሊያም ስትታመም ይደብረዋል። ምክንያቱም እሱ ያገባዉ አይኑ የገባች ቀን ያየዉን ዉበት እንጂ ትክክለኛ እሷነቷን አይደለም። ልትታመም ፣መልኳ ሊቀየር እንደሚችል አያስብም። ልክ እንደሱ ሰዉ መሆኗን ይዘነጋል።
.
አልጋዉ ጥግ ተቀምጬ ሲነጋ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስባለሁ። ሀያት ይሄን ታሪክ ካወቀች ለአይኗ ነዉ የማስጠላት! ራሄል ከእንቅልፏ እስክትነሳ ግጥም ለመፃፍ ስልኬን አበራሁ። የስልኬን ማስታወሻ ከፍቼ መፃፍ ጀመርኩ። ግጥሙን ጨርሼ የፊደል ስህተት ስለቅም ራሄል ከኋላዬ መጥታ ጀርባዬን አቀፈችኝ። ወይኔ አክረም! እጄን ለመጨበጥ ተሳስታ እጇን ከዘረጋች እንዴት ትሳቀቅ እንደነበር እኔ ነኝ የማዉቀዉ። ዛሬ ራቁቴን አቁማ ካየችኝ በኋላ ይኸዉ እንዳሻት በድፍረት ታቅፈኝ ጀመር። ስልኬን ቀምታ ግጥሙን ጮክ ብላ አነበበችዉ።
“አሸነፍሽኝ መሰል ፣ የልብሽ ደረሰ፣
እንቅልፍ ይዞሽ ጠፋ ፣ ፊትሽ ወዝ ለበሰ።
ሴት የማላዉቅ እኔን ፣ ልቤን ሲያርስ አደር ብለሽ ልታወሪ፣
ሀቅን በሴትነት ልታንበረክኪያት ፣ ነገር ልትዘዉሪ።
ነጋልሽ መሸብኝ እልል በይ፣ ተደሰች ግዴለም፣
ከፍ ያለ ይወርዳል የወረደ ይወጣል ፣ ሀሰት ፅኑ አይደለም።
ቆይ ግን ልጠይቅሽ
ከእሳት ስሜትሽ ላይ ፣ ዉሀን እንድቸልስ ምን ሀይል አስገደደኝ?
ገላሽን ላቅፍ ብዬ ፣ ጥፊ እንዴት ቀደመኝ?
ለዉብ ገላሽ ትዕይንት ፣ ለጣፋጭ ከንፈርሽ፣
ምን ይሉት ተዓምር ፣ ወንድነቴ እያለ ንዴቴን ላከልሽ?
ተይዉ አትንገሪኝ፣ መልሱን አዉቀዋለዉ።
ተበዳይ ቢተኛ ለሱ ሚቆምለት፣ ከላይ ጠባቂ አለዉ።”
“ተበዳይ ያልካት ሀያትን እንዳይሆን?” አለችኝ እየሳቀች። “ሰላማዊ ፉክክሩን እኮ ሁለታችንም ተስማምተንበት የጀመርነዉ መሰለኝ። ማሸነፍ መበደል አይሆንም!” አለችኝ። ራሄል ለማሸነፍ የመረጠችዉ መንገድ ምንም ከባድ ቢሆንም እሷ ግን በጣም ጨዋ መሆኗን እኔ እመሰክርላታለሁ። ራሄል ጨዋ ናት! አዎ ራቁ

ቷን ቆማ እንድተኛት ጠይቃኛለች ግን ጨዋ ናት! እዚህ ሁሉ ባለጌ ያስመሰላት ጣጣ ዉስጥ የከተትኳት እኔዉ ነኝ። አንዷን መርጬ አልያም ሁለቱንም አልፈልግም ብዬ ዉሳኔዬን መናገር እየቻልኩ በዝምታዬ የፉክክር ጣጣ ዉስጥ ጨመርኳት። ስለምትወደኝ የሷ ልታደርገኝ ያላትን ሁሉ ተጠቀመች።
“ቁርስ ልዘዝ ወይስ?” አለችኝ ሪቾ ተነስታ እራሷን እያስዋበች
“ኧረ ከሀዩ ጋር ነዉ የምንበላዉ እኔ ዶርም ማደሬን እኮ ነዉ የምታዉቀዉ!” አልኳት።
ተያይዘን ከፓፒረስ ወደ ፔዳ ግቢ ተሳፈርን። ሀሳቤ ቁርስ የምንበላበት ቤት ሆነን እነሀያት ጋር ለመደወል ነበር። ግቢ በር ጋር ከባጃጅ ስንወርድ ከነሀያት ጋር ተገጣጠምን። ሀዩ ፊቷ ቅይርይር አለ። ድንጋጤዬ ምላሴን አሰረዉ። ሀዩ እየሮጠች ሀጅራን እና እኛን በቆምንበት ትታ ወደ ግቢ ገባች። የራሄል እቅድ ሙሉ ለሙሉ ስኬታማ ሲሆን ተሰማኝ። ሀዩን ማጣት የለብኝም። እሷ የወደፊት ህይወቴም ሁሉ መሰረት ናት። በጠየቀችኝ ሰዓት ለማግባት አልፈለግኩም ነበር እንጂ ለትዳር ትክክለኛዋ ሴት ናት። ለምንድነዉ ሳጣት የምረዳት? ለምን?
.
ይቀጥላል…

የጀነራሉ እና የአቢዶ ያልተሰሙ አስገራሚ ገድሎች !!

ያልተሰሙ የ“ጀነራሉ” እና የ“አቢዶ” ገድሎች

➢ ቲም ለማ ላይ ግድያ ለመፈጸም በጌታቸው አሰፋ አዛዥነት የተሰማሩ ሁለት የደህንነት ባልደረቦችን ይዘዉ አስረዋል፡፡
➢ ጌታቸው አሰፋ በአስመላሽ እና አባዱላ አማካኝነት ፓርላማ ዉስጥ የቀበረውን ሴራ አክሽፈዋል፡፡
➢ ታዋቂውን ድምጻዊ ኃጫሉ ሁንዴሳን ከሚሊኒየም አዳራሽ ከደህንነቶች መንጋጋ አስመልጠዋል፡፡
➢ ጌታቸው አሰፋ የሽመለስ አብዲሳ ሰርግ ላይ ድንኳን ሰብሯል፡፡

በቅርቡ የኦሮምያ ክልል በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ፕሬዝዳንት እና የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮምቴ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና እና አቶ አዲሱ አረጋ በቅርብ ጓደኞቻቸዉ የሚጠሩት “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” በሚሉ ቅጽል ስማቸዉ ነዉ፡፡ ሽመልስ “ጀነራሉ” በሚል ቅጽል ስም የወጣለት ቆፍጣና እና ቆጣ ቆጣ እያለ አመራር ስለሚሰጥ እና በዉጤት የሚያምን ስለሆነ ሲሆን አዲሱ ደግሞ ፈጣን፣ ሪስክ የማይፈራ እና የዉሳኔ እና የድርጊት ሰዉ በመሆኑ በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ያገለግል በነበረበት ይሰጣቸዉ በነበሩት ድፍረት የተሞላባቸዉ መግለጫዎች “አቢዶ” የሚል ቅጽል ስም ከትግል አጋሮቹ አሰጥቶታል፡፡ በአፋን ኦሮሞ “አቢዶ” ማለት “እሳቱ” ማለት ነዉ፡፡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ እና በቅርቡ የመለካከያ ሚኒስትር የሆኑት ኦቦ ለማ መገርሳ ሁለቱን ሲጠሯቸው “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” እያሉ እንጂ የሚጠሯቸው ጠርተዋቸው አያውቁም፡፡

ሽመልስ አብዲሳ እና አዲሱ አረጋ ፍጹም የማይለያዩ ተመሳሳይ ዝንባሌ ያላቸዉ፣ እጅግ በጣም በድፍረት የተሞሉ ወጣቶች እንደሆኑ እና ቅርበታቸዉም ከጓደኝነት ያለፈ ፍቅራቸዉም ከወንድማማቾች በላይ እንደሆነ በቅርብ የሚውቋቸው ሰዎች ይመሰክሩላቸዋል፡፡ በፓርቲዉ አባላት ዘንድም በስነ ምግባርም ሆነ በአመራር ብቃታቸዉ የተመሰከረላቸዉ በፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ ተስፋ እና ዕምነት የተጣለባቸዉ ትንታግ ታጋይ ወጣት ምሁራን ናቸዉ፡፡ ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸዉ ቢባል ማጋነን አይሆን፡፡ ፈጽሞ አይለያዩም። ለአብነትም በጅማዉ ጉባዔ የኦዲፒዉ ሊቀመንበር ዶ/ር አቢይ ሁለቱም አንድ መሆናቸዉን ለማሳየት በስብሰባዉ ወቅት ዕድል ሲሰጣቸዉ የአባታቸዉን ስም በማቀያየር ሲጠራቸዉ እንደነበረ አይተናል፡፡ ሽመልስን “ሽመልስ አረጋ”፣ አዲሱን ደግሞ “ አዲሱ አብዲሳ” እያለ ሲጠራቸዉ ነበር፡፡ ሁለቱም አንድ ናቸዉ ለማለት ነዉ፡፡

#ፍልሚያ_1 –

“በጀነራሉ” እና “አቢዶ” አሸናፊነት የተጠናቀቀው በቲም ለማ እና ቲም ጌታቸው አሰፋ መካከል የተካሄደው ፎርሙላ 1 የመኪና እሽቅድድም ውድድር!! በታህሳስ ወር 2010 የ17 ቀናቱ የኢህአዴግ ስብሰባ በተካሄደበት ወቅት ከፍተኛ የኦህዴድ አመራሮች የእስር ማዘዣ ተቆርጦባቸዉ በጥብቅ የመረጃ እና የደህነነት አባላት ጥብቅ ክትትል ስር ወድቀዉ ነበር፡፡ የኦዲፒ ጽ/ቤት እና ፊላሚንጎ ያለዉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤትም በወታደሮች እና በከባድ መሳሪያ በስዉር ተከቦ ነበር፡፡ በተለየ ሁኔታ ክትትል ሲደረግባቸዉ ከነበሩት አመራሮች መካከልም ኦቦ ለማ መገርሳ፣ ዶ/ር አቢይ አህመድ፣ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ፣ ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ አዲሱ አረጋ እና ሽመልስ አብዲሳ ይገኙበታል፡፡ በታህሳስ 2010 በአንዱ ቅዳሜ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም በከተሞች እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ ተመልክተዉ ለክቡር ፕሬዝዳንቱ ሪፖርት እንዲያቀርቡ የክልሉ አመራሮች የስራ ስምሪት ይሰጣቸዋል፡፡

“ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ም ከገላን እስከ አዳማ ከተማ ያለዉን እንቅስቃሴ በመስክ ተመልክተዉ ሪፖርት ለማቅረብ ተቀጣጥረዉ በሌሊት ይገኛሉ፡፡ እንደ ተለመደዉም በጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከሰሩ በኋላ ቁርሳቸዉን ተመግበዉ፣ የ“አቢዶ”ን ተሸከርካሪ ኦዲፒ ጽ/ቤት አቁመዉ በ“ጀነራሉ” አሽከርካሪነት፣ በ“ጀነራሉ” መኪና ጉዟቸዉን ወደ አዳማ ይጀምራሉ፡፡ ገላን ከተማ ደርሰዉ ያለዉን ዝግጅት በአጭሩ ጎብኝተዉ ወደ ዱከም ዘለቁ፡፡ በቲም ጌታቸው አሰፋ በቀጥታ ትዛዝ የሚመሩት የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባላት ዉብሸት ላዉጋዉ እና ለጊዜው ስሙን የረሳሁት ሰው ብርማ ቀለም ባላት ቶዮታ ኮሮላ መኪና የቲም ለማ አባላት የሆኑትን “ጀነራሉ” እና “አቢዶ”ን በቅርብ ርቀት ይከታተሏቸው ያዙ፡፡ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ዱከም የነበረዉን ዝግጅት በአጭሩ ከቃኙ በኋላ ምሳቸዉን በወቅቱ የከተማዉ ከንቲባ ኦቦ ጀባ አዱኛ ጋባዥነት ተመግበዉ ጉዞአቸዉን ወደ ቢሾፍቱ ቀጠሉ፡፡ በገቡበት እየገባች፣ በቆሙበት ስትቆም የነበረችዋ ባለ ብርማ ቀለሟ ቶዮታ አሁንም በቅርብ ርቀት መከታተሏን ቀጥላለች፡፡ እነርሱ ግን ክትትል ስር መሆናቸዉን ልብ ሳይሉ እየሳቁ እየተጫወቱ ጉዟቸውን ቀጥለዋል፡፡ የቢሾፍቱ ጉብኛተቸዉን ጨርሰዉ ወደ ሞጆ እያቀኑ እያለ “ጀነራሉ” በስፖኪዎ ደጋግሞ ከኋላ የምትከተላቸዉን ባለ ብርማ ቀለሟ ቶዮታ መኪና ማየቱ በውስጡ ጥርጣሬ አሳድሮበታል፡፡ “አቢዶ” ጋቢና ሆኖ የተለመደ ቀልድ እና ጨዋታዉን ቀጥሏል፡፡ “ጀነራሉ” ክትትል እየተደረገባቸዉ መሆኑን ቢጠራጠም ዝም ብሎ መኪናዉን ወደ ፊት መንዳቱን ቀጠለ፡፡ ለ“አቢዶ” ምንም ነገር አልነገረዉም፡፡ ጉዙአቸዉን ቀጥለዉ ሞጆ ደረሱ፡፡ ባለ ብርማ ቀለሟ ቶዮታ ኮሮላዋ አሁንም ከኋላቸዉ ናት፡፡ የሞጆ ጉብኝታቸዉን ለመቀጠል ወደ ሰፈር የዉስጥ ለዉስጥ የሚያስገባ መንገድ ሲይዙ ኮሮላዋ አልፋቸዉ ሄደች፡፡ “ጀነራሉ” ም የአጋጣሚ ጉዳይ እንጂ ክትትል እየተደረገባቸዉ እንዳልሆነ በማመን ጉዞዉን ቀጠለ፡፡ የሞጆ ጉብኘት ተጠናቀቆ ወደ አዳማ ጉዞ ሲቀጥሉ ኮሮላዋ የፍጥነት መንገድ መግቢያዉ አካባቢ ቆማ ጠበቀቻቸዉ፡፡ ከኋላ ሆና ክትትሏን ቀጠለች፡፡ ጀነራሉ በተረጋጋ መንፈስ እየሆነ ያለዉን ነገር ለጓደኛዉ ሳይነግር ፍጥነቱን ጨምሮ ወደ አዳማ ተፈተለከ፡፡ የአዳማዉ የመስክ ጉብኝትም በአጭሩ ተጠናቀቀ፡፡ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ፡፡ አሁንም ኮሮላዋ በቅርብ ርቀት አለች፡፡ አዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ ሲገቡ ጀነራሉ መኪናዉን በ180 ፍጥነት አስወነጨፋት፡፡ኮሮላዋ በፍጥነት ለመከታተል ብትሞክርም ከጄኔራሉ የማሽከርከር ብቃት እና የጄኔራሉ ዘመናዊ ተሸርካሪ ጉልበት ጋር እኩል መራመድ ስላልቻለች የአቅሟን ሁሉ ሞክራ ወገቤን አለች፡፡ ጀነራሉ ቱሉ ዲምቱ ሲደርስ በጎሮ መንገድ መሄድ ሲገባዉ በለቡ በኩል ጉዞዉን ቀጠለ፡፡ አዲስ አበባ ሲደርስ ኮሮላዋ ከኋላ አለመኖሯን አረጋገጠ፡፡ ጀነራሉ “ደህንነቶች ሲከታተሉን ነበር፡፡ ጎበዝ ሾፌር በመሆኔ በፍጥነት ቀድሜአቸዉ አስመለጥኩህ፡፡ አንተ መኪናዉን የምትነዳ ቢሆን ኖሮ አስበልተኸን ነበር” ብሎ ለአቢዶ ይነግረዋል፡፡ ሁለቱም ነገሩን እያብሰለሰሉ፣ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸዉ እየተመካከሩ አዲሱ መኪናዉን ወዳቆመበት ወደ ሴንጆሴፍ ት/ቤት ፊት ለፊት ወደ ሚገኘዉ የኦዲፒ ጽ/ቤት ግቢ ይደርሳሉ፡፡ ግቢዉ ዉስጥ ተሰነባብተዉ አዲሱም የራሱን መኪና አስነስቶ ሽመልስን ተከትሎ ከግቢዉ ይወጣሉ፡፡ ከግቢዋ እንደወጡ የሽመልስ አይን ኮሮላዋ መኪና ላይ ያርፋል፡፡ መኪናዋ በጎሮ በኩል ቀድማ መጥታ የኦዲፒ ግቢ አጥር ታካ ወደ ሳሪስ ፊቷን አዙራ ቆማለች፡፡ ሽመልስ ትንሽ አለፍ ካለ በኋላ የኋላ ማርሽ አስገብቶ መንገዱን ዘጋባት፡፡አዲሱም ከኋላ ደርሶ መኪናዋ እንዳንትቀሳቀስ በሚያደርግ መልኩ መንገዱን ዘጋዉ፡፡ ሽመልስ በፍጥነት ከመኪናዉ መዉረዱን ያዩ የደህንነት መስሪያቤቱ ባልደረቦች የመኪናቸዉን መስታወት ወደ መዝጋት ተጣደፉ፡፡ ሽመልስ ሽጉጡን በቀኝ እጁ ይዞ በግራ እጁ የመኪናዋን በር በማንኳኳት “ለምንድነዉ የምትከታተሉን ?” የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ የሁለቱም ደህንነቶች ትኩረት ወደሱ ሆነ፡፡ ሁለቱም “እኛ እየተከታተልናቸሁ አይደለም፡፡ጓደኞቻችን ጋር ለመዝናናት ወደ ሳሪስ እየሄድን ነዉ” የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ በቅጽበት አዲሱ ግራ በሾፌሩ መቀመጫ በኩል ደርሶ “ማንም ሰዉ እንዳይንቀሳቀስ፣ እጅ ወደ ላይ” የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ የደህንነት ባልደረቦቹ እጃቸዉን ወደላይ ከማድረግ ዉጪ ሌላ አማራጭ አልነበራቸዉም፡፡ በዚህ መሃል የኦዲፒ ጽ/ቤት ጥበቃ ልዩ ሃይሎች ደርሰዉ የደህንነት ባልደረቦቹን ቁጥጥር ስር ያዉሏቸዋል፡፡ መኪናዋ ስትፈተሽም የአጭር ርቀት እና የረጅም ርቀት ራዲዮ፣ ገንዘብ፣ ድምጽ ማፈኛ የተገጠመላቸዉ ሽጉጦች ተገኙ፡፡ ሁለቱ የደህነነት ባልደረቦችን አዲሱ ከነመታወቂያቸዉ ፎቶግራፍ አንስቶ በማህበራዊ ሚዲያ እንዲጋለጡ አደረገ፡፡ በቲም ለማ እና ቲም ጌታቸው አሰፋ መካከል የተካሄደው ፎርሙላ 1 የመኪና ሽቅድድም ውድድርም “በጀነራሉ” እና “አቢዶ” አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ በመጨረሻም የጌታቸው አሰፋ ልጆች ቡራዩ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዉ ለ15 ቀናት ምርምራ ሲደረግባቸዉ ከቆየ በኋላ የደህንነት መስሪያ ቤቱ እና የፌዴራል የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት ጫና ከእስር ተፈተዋል፡፡

#ፍልሚያ_2-

በቲም ለማ እና ቲም ጌታቸው አሰፋ መካከል የተካሄደው የቤት ውስጥ (የፓርላማ) ፍልሚያ በቲም ጌታቸው አሰፋ በኩል ተጠባቂ ተጫዋቾች፡- አስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነፍሶ) እና አባዱላ ገመዳ ፤በቲም ለማ በኩል ተጠባቂ ተጫዋቾች፡- “ጀነራሉ” እና “አቢዶ”–)

“ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ከደህንነቶች ጋር ግብ ግብ ገጥመዉ ባሰሩዋቸዉ ጥቂት ቀናት ዉስጥ፣ የታህሳስ ወሩ የኢህአዴግ የ17 ቀኑ ስብሰባ እጅግ ተፋፍሞ ቀጥሏል፡፡ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” የኢህአዴግ ምክር ቤት አባል ስላልነበሩ በስብሰባዉ አይሳተፉም ነበር፡፡ በዚህ ስብሰባ የአዴፓ እና የኦዲፒ አመራሮች በከፍተኛ መናበብ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረዉ የህወሃትን ካምፕ ትንፋሽ ማሳጣት ጀምረዋል፡፡ በዚህ መሃል በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ የነበረዉ መሰሪዉና አይነስዉሩ አስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነፍሶ) አንድ ተንኮል አስቦ ከጌታቸዉ አሰፋ ጋር ይመካከራል፡፡ የአዴፓ እና የኦዲፒ አመራሮች ህብረት ለመበተን ብሎም ትንፋሽ ለማሰባሰብ ብቸኛዉ መንገድ ኦሮሚያ ከፊንፊኔ ስለምታገኘዉ ልዩ ጥቅምን የተመለከተ አጀንዳ መዘርጋት ግድ ነዉ ብሎ ከሌላው መሰሪ ጓዱ ጌታቸዉ አሰፋ ጋር ይመካከራሉ፡፡ ማክሰኞ ዕለት አባይ ነፍሶ የኢህአዴግ ስብሰባ አቋርጦ በመዉጣት “ኦሮሚያ ከፊነፊኔ ስለምታገኘዉ ልዩ ጥቅምን በተመለከተ በሚቀጥለዉ አርብ የፐብሊክ ሂሪንግ ስለሚኖር እንድትገኙ” የሚል ደብዳቤ ይበትናል፡፡ በሚዲያም ያስነግራል፡፡ የአስመላሽ እና የጌታቸዉ አሰፋ ተንኮል የገባቸዉ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” አስቀድመዉ ወደ ስብሰባዉ የሚሄዱ ሰዎችን ማደራጀት እና መቀስቀስ ጀመሩ፡፡ አርብ እለት በጠዋትም ፓርላማ ገብተዉ የኦዲፒ እና የክልሉን መንግስት አቋም በግልጽ አስቀምጠዉ“ የጉዳዩ ባለቤት የኦሮሞ ህዝብ ሳይወያይበት እና ፍላጎቱን ሳይገልጽ፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ሳይቋቋሙ ፐብሊክ ሂሪንጉ መካሄድ የለበትም ” ብለዉ ሽንጣቸዉን ገትረዉ ተከራከሩ፡፡ ከኦዲፒ እና ከአዴፓ የፓርላማ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ በማግኘታቸውም የእነ አስመላሽ ወልደስላሴ (አባይ ነፍሶ) ሴራ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ፡፡ በ“ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ተግባር የተበሳጨው ጌታቸው አሰፋ ለጊዜው ስብሰባውን በሻይ እረፍት እንዲቋረጥ በማድረግ አባይ ነፍሶ እና አባ ዱላ በጌታቸዉ አሰፋ ትዕዛዝ ጉዳዩን አረጋግተዉ ስብሰባዉን እንዲያስቀጥሉ በጌታቸዉ አሰፋ ተላኩ፡፡ አባዱላም አስመላሽን ጎትቶ እየመራ ወደ ፓርላማ አዳራሽ መጥቶ ቁጣ እና ተግሳጽ አወረደ፡፡ ሁለቱን ልጆች ነቀፈ ዘለፈ! “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ወይ ፍንክች ብለዉ በአቋማቸዉ ጸኑ፡፡ እስከ ምሳ ሰዓትም ተከራከሩ፡፡ በመጨረሻም ፓርላማዉ እንዲበተን አደረጉት፡፡ የሻይ እረፍቱ ላይ የአዴፓ አባላትን ሎቢ በማድረግ ከኦዲፓ አባላት ጋር የመከፋፈል ስራ ለመስራት የተሞከረውም ሳይሳካ ቀረ፡፡ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ታላቅ ጀብዱ ባይፈጽሙና ይህን ለዘመናት የሚያስመሰግናቸውን አኩሪ ተግባር ባይከውኑ ኖሮ የአዴፓ እና የኦዲፒ ጥምረት እና መናበብ ገድል ይገባ ነበር፡፡ የ17 ቀኑ ስብስባ ላይ የታየውም የአዴፓ እና የኦዲፒ ጥምረትም የፓርላማው ቀጣይ ክፍል ነው፡፡ አሁን የደረስንበትንም ለዉጥ በህወሃት ሴራ ምክንያት አናየዉም ነበር፡፡

#ፍልሚያ_3-

በቲም ለማ እና ቲም ጌታቸው አሰፋ መካከል የተካሄደው 3ተኛው የቤት ውስጥ ፊልሚያ (ሚሊኒዬም አዳራሽ) ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉት ወገኖች በሃጫሉ ሁንዴሳ እና በሌሎች የኦሮሞ አርቲስቶች አስተባባሪነት ወገን ለወገን (Lammin lammif) የሚል የሙዚቃ ኮንሰርት ተዘጋጅቶ ነበር፡፡በ OBN ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ባገኘው በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ሃጫሉ ሁንዴሳ “ጅርቱ” በሚል ርዕስ ያቀረበው በሽለላ የታጀበ በድፍረት የተሞላ ስሜትን የሚያነሳሳ ሙዚቃ ብዙዎች ከመቀመጫቸው ተነስተው አጨብጭብውለታል፡፡ ሃጫሉ ከፍተኛ የኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ ከፊቱ ቁጭ ብለው ይሄን ሙዚቃ በመጫወቱ በበርካቶች ከፍተኛ አድናቆትን አስገኝቶለታል፡፡ ሃጫሉ በዘፈኑ ሚሊዮኖችን ቢያስደስትም ጥቂቶቹ ግን ተከፉበት፡፡ በተለይ ሃጫሉ በዕለቱ በዘፈኑ ውስጥ “ፈረስህን ያዝና አራት ኪሎ ግባ ለ 4ኪሎ የምትቀርበው አንተ ነህ” የሚለው ስንኝ ጌታቸው አሰፋ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ በገፍ ያስገባቸው የደህንነት አባላትን አስቆጣ፡፡ ተቆጥተው አልቀሩ ሃጫሉ ሁንዴሳን ከሚሊኒየም አዳራሽ አፍነው ለመውሰድ በህቡዕ መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ ድንገት ግን እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ሃጫሉ ጠፋ፡፡ ራሱ ሃጫሉ አይደለም.. ሃጫሉን አየሁ የሚል ሰውም ጠፋ፡፡ ህልም በሚመስል መልኩ ሃጫሉ ከአይናችው ስር ተሰወረ፡፡ ይሄን ጀብዱ አሁንም የፈጸሙት “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ናቸው፡፡ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ከሚሊኒዬም አደራሽ በተጠና እረቂቅ ዘዴ ጀግናውን ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳን በስውር በማስመለጥ ለምሳ ሲያስቡን ለቁርስ አደረጓቸው፡፡ በእነዚህ የቁርጥ ቀን ልጆች አማካኝነት ቲም ለማ ቲም ጌታቸው አሰፋ ላይ ሀትሪክ ሰራ፡፡ (ሃጫሉ ሁንዴሳ OBN ቴሌቪዥን ቀርቦ ያስመለጡኝ ሽመልስ እና አዲሱ ናቸው በማለት መስክሮላቸዋል፡፡)

#ቦነስ_ፍልሚያ፡- ድንኳን ሰባሪው ጌታቸው አሰፋ
ፓርላማዉን ከበተኑ በኋላ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” ላይ በደህንነት የሚደረግባቸዉ ክትትል እና ጫና በረታ፡፡ ሆኖም በሁለት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ማለትም ጥር 6/2010 የሽመልስን ሰርግ መደገስ ነበረባቸዉ፡፡ ይህን ሁሉ ጫና ተቋቁመዉ ከደህነነት እና ከጸጥታ አካላት ጋር እየተናነቁ፤ ትከሻ ለትከሻ እየተገፋፉ ግማሽ ዘመድ አዝማድ ግማሽ ደህንነት እና የጸጥታ ስኳድ ክትትል አድራጊዎች በተገኙበት የ “ጀነራሉ” ሽመልስ አብዲሳ ሰርግ በደማቅ ስነስርዓት ተፈጸመ፡፡ ጀግናዉ ሃጫሉ ሁንዴሳም የሰርግ ስነ ስርዓቱ አድማቂ ፈርጥ ነበር፡፡

#እንደ_ማሰረጊያ…

ለህዝባቸው እና ለሀገራቸው እንዲህ የተፋለሙትን ጀግኖች ማገዝ፣ ሲሳሳቱ ማረም እንጂ መፋለም አስፈላጊ አይደለም፡፡ በእሳት ተፈትነው ስለወጡ በጭብጨባ እና በተቀናጀ ስም ማጥፋት ገሸሽ እናደርጋቸዋለን ብሎ ማሰብም የዋህነት ነው፡፡ “ጀነራሉ” እና “አቢዶ” በኦሮሞነታቸው የሚኮሩ (sabbonumaa) ብቻ ሳይሆኑ ኮርተው የሚያኮሩ ልንኮራባቸው የሚገቡ ልጆቻችን ናቸው፡፡

ከጎናቸው በመቆም እናግዛቸው፡፡
.

አራቱ ሚስቶች

አራት ሚስቶች የነበሩት አንድ ሀብታም ነጋዴ ነበር፡፡ አራተኛ ሚስቱን ከሌሎች አብልጦ በእጅጉ ይወዳታል፡፡ ስለሚወዳትም ጥሩውን ሁሉ ለእርሷ በመስጠት ይንከባከባታል፤ያስደስታታል፡፡ ሦስተኛ ሚስቱን መውደድም ብቻ አደለም ይኮራባታል፣ ይመካባታልም ጭምር፡፡ ይዟት በአደባባይም ለመታየት ይፈልጋል ነገር ግን ጥላው እንዳትሄድ በጣሙን ይሰጋል፡፡ ሁለተኛ ሚስቱንም እንዲሁ ይወዳታል፡፡ ይች ሁለተኛ ሚስቱ በነገሮች አስተዋይና ብልህ ታጋሽም በመሆኗ ይመካባታል፡፡ ነጋዴው አንዳች እክል የገጠመው እንደሁ ችግሩን ታቅፎ እሚያመራው ወደ ሁለተኛ ሚስቱ ነው ፡፡ እሷም በአስቸጋሪው ሰዓት ከጭንቀቱ ትገላግለዋለች፡፡ የመጀመሪያ ሚስቱ በጣም ታማኝ አጋሩ ናት፡፡ ቤቱንና ንግዱን የምትመራለትና የምታስተዳድርለት እሷው ነች፡፡ እሷ በጣም የምታፍቅረው ቢሆንም እሱ ግን ስለማያፈቅራት አንድም ቀን በትውስታው ውስጥ ቦታ ሰጥቷት አያውቅም ነበር፡፡

ታዲያ አንድ ቀን ህመም ተሰማውና ማለፉን ባሰበ ጊዜ የተድላ ዓለሙን እያስታወሰ እንዲህ አሰበ “አራት ሚስቶችና የተትረፈረፈ ሀብት አለኝ ነግር ግን በሞት ጊዜ ብቻየን እሆናለሁ፡፡ እንዴት ብቻየን እሆናለሁ?” በማለት አራቱንም ሚስቶች በማስጠራት ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡

“ሁላችሁንም በጣም እወዳችኋለሁ:: የሚያምሩ አልባሳትንም እያለበስኩ ሳስጌጣችሁ ኖርኩ፡፡ አሁን ግን ልሞትናውና ከብቸኝነቴ ታድኑኝ ዘንድ ተከተሉኝ” አላቸው፡፡ አራተኛው ሚስቱ “በፍጹም አይሆንም” ስትል መልሱን ሰጥታው ከአካባቢው ተሰወረች፡፡ ነጋዴው በሰማው ምላሽ ልቡ ተነካ፡፡ ለሦስተኛዋ ሚስቱ “በሕይዎቴ ሙሉ ስወድሽ ኑሪያለሁ አሁን አብረሽኝ ልትሆኝና ወደምሄድበት ልትከተይኝ ትፈቅጃለሽ?” አላት በአዘኔታ ሁኖ መልስ ሲጠባበቅ “አይሆንም ሕይዎት አትጠገብም ፡፡ እዚህ መኖር መልካም ነው፡፡ እናም ከአንተ ሞት በኋላ አግብቸ መኖር እሻለሁ” አለችው፡፡ ይህ ሀብታም ነጋዴ ልቡ ዝቅ ሲልና ወደ ቀዝቃዛነት ሲለወጥ ተሰማው፡፡ አሁንም በተስፋ መቁረጥ ሁኖ “በሕይዎቴ ሙሉ እርዳታን ስፈልግ ወደ አንች ስመላለስ ኑሪያለሁ፡፡ ስትረጅኝም ነበር፡፡ አሁንም እርዳታሽን ፈልጊያለሁና እርጅኝ” ሲል ሁለተኛ ሚስቱን ጠየቃት፡፡ “በዚህ ሰዓት ልረዳህ ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡ ማድረግ የምችለው አንተን ወደ መቃብርህ መሸኘት ብቻ ነው” ስትለው መብርቅ የመታው ያህል ክው አለ፡፡ በድንጋጤ ስሜት ተውጦ እያለ “የትም ብትሄድ እከተልሃለሁ፤ አንተጋ እሆናለሁ!” የሚል ድምጽ ሲያስተጋባ ተሰማው ዓይኑን ሲያነሳ የተጎሳቆለ እይታ ያላት የመጀመሪያ ሚስቱ ነበረች ነጋዴው ሳግ እየተናነቀው “ሲኖረኝና ስችል ልንከባከብሽ ይገባኝ ነበረ” በማለት እቅፍ አድርጎ ወደሰውነቱ አስጠጋት፡፡

በመሠረቱ ሁላችንም በሕይዎታችን አራት ሚስቶችን አኑረን ይሆናልና የእኛም ታሪክ ሊሆን ይችላል፡፡

1. አራተኛው ሚስታችን ፈራሹ ስጋችን ነው፡፡ ለምቾቱና ለውበቱ ተጨንቀን ብንደክምም ቀሪ እንጅ ተከትሎን አይሄድም፡፡

2. ሦስተኛው ሚስታችን አለን የምንለው ነገር ንብረት፣ ሀብትና ክብራችን ነው፡፡ ይሄም እኛ ስንሞት ወደሌሎች የሚተላለፍ ነው፡፡

3. ሁለተኛው ሚስታችን ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመናችን የቱንም ያህል ቀረቤታና ቁርኝት ቢኖረንም ማድረግ የሚችሉት እስከ መቃብር መሸኘት ብቻ ነው፡፡

4. የመጀመሪያዎ ሚስታችን ሕያው ነፍሳችን ናት፡፡ ቁስና ሀብት ስናሳድድ ወደ ጎን ገፍተናት ቢሆንም አብራን የምትሆነው እሷው ነችና በመጨረሻው ሰዓት ሳይሆን አሁኑኑ እንድናለመልማት ያስፈልጋል ነው ያታሪኩ ጭብጥ፡፡

ምንጭ፡ The Four wives